TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← Elyas tube
Elyas tube avatar

TGINSIGHT POST

Post #56

@ethiotech20

Elyas tube

Peržiūros90Peržiūrų skaičius
Paskelbta09-102025-09-10 12:34
Turinys

Įrašo turinys

በስተመጨረሻም Apple ሲጠበቅ የነበረውን iPhone 17 series ለቋል። IPhone 17 Iphone 17 A19 chip ተካቶበት በአምስት አይነት የcolor አማራጮች ለገበያ ውሏል። Iphone 17 ቻርጅ ተደርጎ 50% battery ለመድረስ 20 ደቂቃ እንደሚፈጅበት ተገልጿል። በተጨማሪም በ256 GB storage እንዲሁም 48 megapixel dual-fusion ካሜራ ተገጥሞለታል። እንዲሁም 6.3 ኢንች display size ዋጋውም ከ799 ዶላር ጀምሮ ይሸጣል። IPhone 17 Air ሌላኛው ሲጠበቅ የነበረው ስልክ IPhone 17 Air ነው። ይህ አዲስ የተወቀ ስልክ እስካሁን Apple ካመረታቸው ስልኮችም ቀጭኑና ቀላሉ ነው። 5.6mm ውፍረትና 6.5 ኢንች display size አለው። A19 Pro chip እና 48 megapixel fusion ካሜራ ተገጥሞለታል። ቻርጅ እያደረገ 50% ለመድረስም 30 ደቂቃ የሚወስድ ሲሆን ዋጋውም ከ999 ዶላር ጀምሮ ይሸጣል። IPhone 17 Pro ይህ ስልክ A19 pro chip ተገጥሞለት በ6.3 ኢንች display size ከመቅረቡም በተጨማሪ 48 MP Fusion Main, 48MP Fusion Ultra Wide እና 48MP Fusion Telephoto camera አለው። ዋጋውም ከ1099 ዶላር ጀምሮ ነው። IPhone 17 pro max ከIphone 17 pro ጋር ቢቀራረብም 6.9 ኢንች display size አለው። ሁሉም ሞዴሎች iphone 17 ሞዴሎች 120 hz ProMotion display እና 18 megapixel front camera አላቸው።