Įrašo turinys
Instagram 3 ቢልዮን Active user አፈራ። የmeta CEO mark zukerberg እንደገለፀው ከሆነ Instagram 3 ቢልዮን ወርሀዊ ንቁ ተጠቃሚ ወይም Active users ማግኘት ችሏል። Meta ኢንስታግራምን በ2012 በ1 ቢልዮን ዶላር መግዛቱ አይዘነጋም። አንድዳንድ አስገራሚ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ቁጥራዊ መረጃዎች በ1997 እንደፈረንጆች አቆጣጠር ጅማሮውን ያደረገው ማህበራዊ ሚዲያ አኗኗራችንን እና የእርስበርስ መስተጋብርጅራችንን ሙሉ ለሙሉ ለውጦታል። ⚫ዛሬ ላይ በአለም አቀፍ ደረጃ 5.41 ቢሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ወይም 65.7% የሚሆነው የዓለም ህዝብ ማህበራዊ ሚዲያን ይጠቀማል። ⚫አማካኝ ዕለታዊ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም 2 ሰአት ከ40 ደቂቃ ነው። ⚫አንድ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ በአማካኝ 6.8 የsocial media አካውንቶች አሉት። ⚫የማህበራዊ ሚዲያ የሚጠቀሙ ሰዎች ቁጥር በየአመቱ በአማካይ 4.7% ጭማሪ ያሳያል። በየሰከንዱ 7.6 አዳዲስ ሰዎች ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይመዘገባሉ። ⚫ ማህበራዊ ሚዲያን ከሚጠቀሙት ውስጥ 75% የሚሆኑት ከ13 ዓመት በላይ ናቸው። ⚫ 95.7% የሚሆኑት ኢንተርኔትን አዘውትረው የሚጠቀሙ ሰዎች የማህበራዊ ሚዲያም ተጠቃሚ ናቸው። ⚫የአለም ህዝብ በየቀኑ 14.5 ቢሊዮን ሰአት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያሳልፋል። ያ ማለት 17 ሚሊዮን አመታት በየቀኑ ማህበራዊ ሚዲያ በመጠቀም ያልፋል። ምንጭ: datareportal.com ✍️እናንተ ስንት ማህበራዊ ሚዲያ አካውንት አላችሁ?