@borkena · Post #5862 · 26.02.2026 г., 06:33
አቶ ጋሻው እነ ክርስቲያን ታደለ እና ደሳለኝ ጫኔን የአማራ ታጋይ ሳይሆኑ የሻዕቢያ ተወካዮች ናቸው ሲሉ ወነጀሉ። የአብን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆኑት አቶ ጋሻው መርሻ ዶክተር ደሳለኝ ጫኔን በስነ ምግባር ጉድለት ፈርጀዋል። አቶ ጋሻው መርሻ ከቢቢሲ ጋር እያደረጉት የነበረውን ቃለ ምልልስ ማቋረጣቸው አነጋጋሪ ሆኗል ጋሻው ባልተቋጨው ቃለመጠይቃቸው ላይ ዶክተር ደሳለኝ ጫኔን፣ ዶክተር አበባው ደሳለው እና አቶ ክርስቲያን ታደለን በስነ ምግባር ጉድለት ከሰዋቸዋል። የአብኑ አመራር እነዚህን ሰዎች በሥነ ምግባር ግድፈት ከፓርቲው የተባረሩ ናቸው ብለዋል። ሲያራምዱ የነበረው የፓርቲውን አቋም ሳይሆን የራሳቸውን የግለሰብ አቋም ነው በማለት ወንጅለዋቸዋል። ጋሻው ያባረርናቸው በሥነ ምግባር ጉድለት ነው። የሚያደርጉት ትግልም ለአማራ ሕዝብ የሚደረግ ትግል ነው ብለን እንደ ፓርቲም አናምንም፤ እኔም እንደ ግለሰብ አላምንም። የሻዕቢያን የውክልና እንቅስቃሴ ነው የሚያካሂዱት ሲሉ ተናግረዋል። የአማራ ሕዝብ ትግልን መሳታቸውን በግልጽ ነግረን ከፓርቲው አባረናቸዋል በማለት ገልፀዋል። #Ethiopia#Ethiopiannews#news#ANM#አብን#ዜና