@ebcnewsnow · Post #53078 · 06.04.2026 г., 14:20
በደቡብ ኢትዮጵያ 1.6 ቢሊዮን ብር ፈሰስ የተደረገባቸው የሶላር ሚኒግሪድ ኃይል ማመንጫዎች ሥራ ጀመሩ ******************* በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ የሶላር ሚኒግሪድ የኃይል ማመንጫዎች ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ እንደገለጹት፣ ፕሮጀክቶቹ በደቡብ ኦሞ ዞን (ሳላማጎ፣ ሐመር፣ ዳሰነችና ኦሞራቴ) እንዲሁም በጋሞ ዞን (ጋርዳ ማርታ ወረዳ) የሚገኙ ከ20 ሺህ በላይ አባወራዎችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ያደርጋሉ። ማመንጫዎቹ በጥቅሉ 2 ሺህ 325 ኪሎዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ያላቸው ሲሆን፤ ግንባታቸውም በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና በዓለም ባንክ ትብብር የተከናወነ መሆኑ ተገልጿል። አቶ ጥላሁን የገጠሩን ማህበረሰብ የአማራጭ ኃይል ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁመው፤ ኅብረተሰቡ የተገነቡ የኃይል መሠረተ ልማቶችን በባለቤትነት እንዲጠብቅ አሳስበዋል። ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2030 ሁሉንም ዜጎቿን የታዳሽ ኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል እቅድ ነድፋ እየሠራች ትገኛለች። የሶላር ሚኒግሪድ ኃይል ማመንጫዎች ሥራ ጀመሩ በተመስገን ተስፋዬ #Ethiopia#renewableenergy#greenenergy#EBC#ebcdotstream