@ebcnewsnow · Post #52848 · 28.03.2026 г., 18:58
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የ50 ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓሉን በታላላቅ የምረቃና የዐውደ ርዕይ ኩነቶች አከበረ ************************** ግማሽ ክፍለ ዘመን ያስቆጠረውን የስኬት ጉዞ በተለያዩ ተግባራት እያከበረ የሚገኘው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን፣ ዛሬ ሶስት አበይት ኩነቶችን በይፋ አከናውኗል፦ ✅ ልዩ የፎቶግራፍ ዐውደ ርዕይ፦ የኮርፖሬሽኑን የ50 ዓመት የልማትና የዕድገት ታሪክ የሚያሳይ የፎቶግራፍ ዐውደ ርዕይ ተከፍቷል። ✅ ዘመናዊው "ጎልድ ሞል" ምረቃ፦ በፒያሳ መሀል ለወርቅ ንግድ ሱቆች አገልግሎት እንዲውል ተደርጎ የተገነባው ዘመናዊ የንግድ ሕንፃ ተመርቋል። ✅ የ27 ወለል ሁለገብ ሕንፃ ምረቃ፦ በሱማሊ ተራ አካባቢ ያስገነባው፣ 3 ቤዝመንት፣ ምድር ቤት እና 23 ወለሎች (3B+G+23) ያሉት እጅግ ዘመናዊ ሁለገብ ሕንፃ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል። እነዚህ ስኬቶች የኮርፖሬሽኑን ለሀገር ልማትና ለከተማ ውበት ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ያሳያሉ። እነዚህ ሁነቶች በምስል ይመልከቱ፦ #FHC50Years#GoldJubilee#Ethiopia#AddisAbaba#Inauguration