@ebcnewsnow · Post #53540 · 14.04.2026 г., 18:04
ኢትዮጵያ ዓለም እያመራበት ያለውን የ"ኢንዱስትሪ 4.0" እውነታ በንቃት እየተገበረች ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ********************** ዓለም አቀፉ የኢንዱስትሪ ገጽታ ከጭስ እና ብረት ወጥቶ በዳታ፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እና አረንጓዴ ኢነርጂ እየተመራ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢቢሲ ጋር ባደረጉት ሰፊ ቃለ-መጠይቅ፣ ዓለም እያመራችበት ያለውን የ"ኢንዱስትሪ 4.0" እውነታ ኢትዮጵያ በንቃት እየተገበረችው መሆኑን አስታውቀዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ በጂኦ-ፖለቲካዊ ውጥረቶች የተነሣ የአቅርቦት ሰንሰለቶች እየተቆራረጡ እና "ፕራግማቲዝም" ወሳኝ መፍትሔ በሆነበት በአሁኑ ወቅት፣ ኢትዮጵያ የነፃ ንግድ ቀጣናዎችን ከደረቅ ወደቦች ጋር በማስተሣሠር የሎጂስቲክስ መሠረቷን እያጠናከረች ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። ከዚህም ባለፈ ኢትዮጵያ በዜሮ ፍሳሽ ማጣሪያ እና በንፁህ የታዳሽ ኃይል ማምረት መቻሏ በርካታ ዓለም አቀፍ የሶላር እና የአልሙኒየም አምራቾችን እየሳበ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። ሀገራችን ያለፈውን ሥርዓት ስህተቶች (አክሳሪ ኢንቨስትመንቶች እና የሀብት ብክነት) በማረም፣ አጭር ጊዜ ውስጥ ሀብት በሚመልሱ ፕሮጀክቶች (እንደ ማዳበሪያ ፋብሪካዎች) እና በከተሜነት ላይ ትኩረት አድርጋ ዘላቂ የኢኮኖሚ ልማትን እያረጋገጠች ትገኛለች ነው ያሉት። #EBC#Ethiopia#PMAbiyAhmed#Industry4#GreenEnergy#RenewableEnergy#Logistics#FreeTradeZone