@ebcnewsnow · Post #51539 · 08.02.2026 г., 11:21
ዕውቀትና ቴክኖሎጂ የተጣመሩበት የሙሐመድ ቢን ዛይድ ኤአይ ዩኒቨርሲቲ ******************************* የዓለም የኢኮኖሚና የቴክኖሎጂ አድማስ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) መሪነት አዲስ መልክ እየያዘ ይገኛል። ይህንን ተለዋዋጭ እውነታ ቀድማ የተረዳችው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ በአቡ ዳቢ የሙሐመድ ቢን ዛይድ ኤአይ ዩኒቨርሲቲን (MBZUAI) በመገንባት ለዘርፉ መሠረት የሚጥል ሥራ እያከናወነች ነው። ተቋሙን ልዩ የሚያደርጉት ነጥቦች፦ መገኛ፦ በአቡ ዳቢ መስዳር ሲቲ (Masdar City) የሚገኝ ስትራቴጂካዊ የምርምር ማዕከል ነው። ልዩነት፦ በዓለም የመጀመሪያው በኤአይ (AI) ምርምር ላይ ብቻ ያተኮረ ዩኒቨርሲቲ ነው። ተደራሽነት፦ በአሁኑ ወቅት ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የተውጣጡ ከ300 በላይ የድህረ-ምረቃ ተማሪዎችን እያሰለጠነ ይገኛል። ትኩረት፦ በኮምፒውተር ቪዥን፣ በማሽን ለርኒንግ እና በተፈጥሮ ቋንቋ ማቀነባበሪያ (NLP) ዘርፎች ላይ ያተኩራል። አቅም፦ የከፍተኛ ፍጥነት ኮምፒውቲንግ (Supercomputing) እና ዘመናዊ የላብራቶሪ መሣሪያዎችን የታጠቀ ነው። የኢትዮጵያ ቀጣይ እርምጃ፦ ኢትዮጵያም ይህንን ዓለም አቀፋዊ የቴክኖሎጂ አቅጣጫ በመከተል፣ በዓለም ሁለተኛው የሆነውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ በአንድ ዓመት ውስጥ ወደ ሥራ እንደምታስገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መግለጻቸው ይታወሳል። ወጣቶችን ለነገው የቴክኖሎጂ ውድድር ማዘጋጀት የወቅቱ ወሳኝ ተግባር በመሆኑ፣ የሚቋቋመው ዩኒቨርሲቲ ለሀገርና ለትውልዱ ያለው ፋይዳ እጅግ የላቀ እንደሚሆን ይጠበቃል። #EthiopianBroadcastingCorporation#UAE#AI#University#MBZUAI#Ethiopia#TechNews