@ebcnewsnow · Post #52383 · 14.03.2026 г., 16:29
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ለሜቄዶኒያ የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ ****************** የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮችና ሠራተኞች በዛሬው ዕለት በሜቄዶኒያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል በመገኘት የ5 ሚሊየን ብር ድጋፍና የማዕድ ማጋራት መርኃ ግብር አከናውነዋል፡፡ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት በዚሁ ወቅት፤ ተቋማቸው ከመደበኛ የመንግሥት ሥራው ባለፈ በተለያዩ ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳትፎ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰዋል። ለሜቄዶኒያ መሥራች አቶ ቢኒያም በለጠና ለሥራ ባልደረቦቹ ባስተላለፉት ምስጋናም "ኢትዮጵያ ታመሰግናችኋለች" ሲሉ አድናቆታቸውን ገልጸዋል። የዛሬው ድጋፍ የአንድ ወቅት ብቻ ሳይሆን፣ ተቋሙ በቋሚነት ለሜቄዶኒያ ድጋፍ የሚያደርግበትን መንገድ እያመቻቸ መሆኑን ወ/ሮ ሰላማዊት ጠቁመዋል። የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ያከናወነው ይህ የበጎ አድራጎት ተግባር፣ የመንግሥትም ሆኑ የግል ተቋማት ለማኅበራዊ ኃላፊነት ሊሰጡት የሚገባውን ትኩረት የሚያሳይና ለሌሎችም አርአያ የሚሆን ተግባር መሆኑ ተገልጿል። በሔለን ተስፋዬ #EthiopianBroadcastingCorporation#Ethiopia#Charity#SocialResponsibility#MaedMagarat