@ebcnewsnow · Post #52969 · 03.04.2026 г., 08:55
ለመመዝገብ የቀሩት 3 ቀናት ብቻ ናቸው!!!! ********************* ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ሊጠናቀቅ ሦስት ቀናት ብቻ ቀርተዋል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት፣ የመራጮች ምዝገባ እስከ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ይቆያል። የምዝገባው ሂደት ሊጠናቀቅ 3 ቀናት ብቻ ስለቀሩት፣ እስካሁን የምርጫ ካርድ ያልወሰዳችሁ ዜጎች ቀሪዎቹን ቀናት እንድትጠቀሙ እናስታውሳለን። ምርጫ ካርድ አለመውሰድ የራስዎን እና የቤተሰብዎን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ሌላ አካል እንዲወስን በራስዎ ፈቃድ ዕድሉን አሳልፎ መስጠት ነው። በሀገርዎ የዴሞክራሲ ልምምድ ውስጥ ለመወሰን እና የዜግነት ግዴታዎን ለመወጣት የድምፅ መስጫ ካርድዎን ይያዙ። ድምፅ መስጠት መብትዎ ብቻ ሳይሆን የዴሞክራሲ ተሳትፎዎ መገለጫ ነው። በሚቀርብዎ የምርጫ ጣቢያ በአካል በመገኘት ወይም በምርጫዬ መተግበሪያ በዲጂታል አማራጭ መመዝገብ ይችላሉ። ምርጫዬ መተግበሪያን፦ ለአንድሮይድ (Play Store): https://play.google.com/store/apps/details.. ለአይፎን /iOS/ (App Store): https://apps.apple.com/us/app/mirchaye/id6756587049 በድረ-ገጽ https://mirchaye.portal.nebe.org.et/ ጊዜው ሳይረፍድ ዛሬውኑ ካርድዎን ይውሰዱ፤ በምርጫ ብቻ ለውጥ ያምጡ። #Ethiopia#Election2026#VoterRegistration#VoteEthiopia