@ebcnewsnow · Post #51949 · 28.02.2026 г., 06:55
ምርጫ - የነገን ብሩህ ተስፋ ለመቅረጽ የሚያስችል ቁልፍ መሣሪያ ****** ታላቁ የሰላም ተምሳሌት ኔልሰን ማንዴላ "ምርጫ የተሻለች ዓለምን ለመገንባት በእጃችን ያለ ታላቅ ዕድል ነው" የሚል አባባል ነበራቸው። ይህም የምርጫ ድምፃችን ከማንኛውም ቁሳዊ ኃይል ይልቅ የነገን ብሩህ ተስፋ ለመቅረጽ በእጃችን ያለ ዋነኛ ቁልፍ መሣሪያ መሆኑን ያሳያል። መራጭ መሆን መብት ብቻ ሳይሆን ለሀገርና ለሚመጣው ትውልድ የሚደረግ ታላቅ የዜግነት ኃላፊነት ነው። በምንሰጠው ድምፅ ፍትሕን፣ ልማትንና ሰላምን የመገንባት አቅም አለን። የምርጫ ድምፃችን የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ መሠረት ነው። ስለዚህ ታሪክን የዴሞክራሲ ታሪክን በጎ መልኩ ለመገንባት እያንዳንዱ ድምፅ የራሱ የሆነ ክቡር ዋጋ እንዳለው ተገንዝበን፣ በበሰለና በኃላፊነት ስሜት መሳተፍ ይገባል። ምርጫ የግለሰቦች ውድድር ሳይሆን የጋራ ቤታችንን የምናድስበት የጋራ ራዕያችን ነው! እኔ የምርጫ ጉዳይ ያገባኛል፣ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እሳተፋለሁ! እርስዎስ? በጌትነት ተስፋማርያም #EBC#Election2018#Ethiopia
Hashtags