@rednile12 · Post #10814 · 20.01.2026 г., 13:25
በ2020ው የዋሽንግተን ረቂቅ የስምምነት ሰነድ አሜሪካ እና ግብፅ እንደ ወጥመድ የተጠቀሙት "DROUGHT" እና "WATER FLOW" ዋሽንግተን ላይ ተደርጎ በነበረው ድርድር የአየር ሁኔታን ተገን አድርገው ግብፅ እና አሜሪካ "Historic Right" የሚለውን የግብፅን የቅኝ ግዛት ትሪክት " #DROUGHT" የሚል ካባ አልብሰው በ2020ው የዋሽንግተን ረቂቅ የስምምነት ሰነድ ውስጥ እንደት እንዳስገቡ እንመልከት ወደ ዋሽግተኑ ረቂቅ የስምምነት ሰነድ ከመሄዳችን በፊት ትራምፕ ጃንዋሪ 16፣ 2026 ላይ “በድርቅ እና ለረጅም ጊዜ ደረቅ ዓመታት ለግብፅ እና ለሱዳን የሚለቀቁ የውሃ ልቀት ሊተነብይ የሚችል ይሆናል” ብሎ ለፍሬንዱ አል ሲሲ የላከውን መልዕክት ስንመረምር መልዕክቱ የተቀዳችው ከረቂቅ ሰነዱ ይሆን🤔? የሚል ጥርጣሬም ያጭራል:: ጥርጣሬውን እንደጥርጣሬ ይዘን👇 በ2020 የዋሽንግተን ረቂቅ ሰነድ ውስጥ የሰፈሩት “ድርቅ” እና “ረዥም ጊዜ ደረቅ ዓመታት” ለሚሉ አባባሎች፤ ኢትዮጵያ አባባሎቹ አደገኛ ወጥመድ ናቸውና ከትርጓሜያቸው ጀምሮ መስተካከል አለባቸው ስትል ተከራክራለች:: 🔻Continued Below @rednile12
Hashtags