@ebcnewsnow · Post #51412 · 01.02.2026 г., 11:46
📍 ኢትዮጵያና ዩናይትድ ኪንግደም በኃይል መሰረተ-ልማት ግንባታ ላይ አዲስ ስምምነት ተፈራረሙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዩናይትድ ኪንግደም የውጭ፣ የኮመንዌልዝ እና የልማት ጉዳዮች ሚኒስትር ይቬት ኩፐር ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል። የውይይቱና የስምምነቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦ 🔹 ዲፕሎማሲያዊ ውይይት፦ መሪዎቹ በቁልፍ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ምክክር አድርገዋል። 🔹 የኢንቨስትመንት ትብብር፦ በኢንቨስትመንት እና በሀብት አስተዳደር የቴክኒክ ትብብር ለማድረግ የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል። 🔹 የኃይል ማስተላለፊያ ፕሮጀክቶች፦ ሁለት ግዙፍ የኃይል ማስተላለፊያ ፕሮጀክቶችን ወደ ተግባር የሚያስገቡ የልማት ስምምነቶች ተፈርመዋል። እነርሱም፦ የሁርሶ-አይሻ (400 ኪሎ ቮልት) እና የደገሃቡር-ቀብሪደሃር (132 ኪሎ ቮልት) ፕሮጀክቶች ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እነዚህ ስምምነቶች በሀገራቱ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር እና ስትራቴጂካዊ መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት ረገድ ትልቅ እርምጃ መሆናቸውን ገልጸዋል። #Ethiopia#UK#PMAbiyAhmed#EnergyInfrastructure#Diplomacy#ኢትዮጵያ