@ebcnewsnow · Post #51219 · 23.01.2026 г., 14:11
በደቡብ ጎንደር ዞን ታች ጋይንት በጫካ ሲንቀሳቀስ የቆየው ታጣቂ ቡድን የሰላም ጥሪውን ተቀበለ *************** በአማራ ክልል መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል የተደረሰውን አዲስ የሰላም ስምምነት ተከትሎ ራሱን "የገብርየ ክፍለ ጦር" በማለት ሲጠራ የቆየው ታጣቂ ቡድን የሰላም ጥሪውን ተቀብሏል። በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር ዞን ታች ጋይንት ወረዳ፣ በጫካ ሲንቀሳቀስ የቆየው ታጣቂ ቡድኑ፤ የመንግሥትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ተመልሷል። ይህ ውሳኔ በክልሉ ለረጅም ጊዜ የቆየውን የትጥቅ ግጭት በውይይትና በሰላም ለመፍታት የተያዘውን አዲስ አቅጣጫ በተግባር መሬት ያወረደ ትልቅ እርምጃ ሆኖ ተመዝግቧል። ለቡድኑ አባላት በተዘጋጀው የአቀባበል መርሐ ግብር ላይ የደቡብ ጎንደር ዞን የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ መንበር ክፈተው፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ መገኘታቸውን የአማራ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል። #Ethiopia#PeaceAgreement#AmharaRegion#SouthGondor#Peace