@ebcnewsnow · Post #54156 · 30.04.2026 г., 17:42
"ኢትዮጵያ ለእኛ በምናብ የምትሣል ሕልም ብቻ ሳትሆን በተግባር የምትገነባ እውነታ ናት።" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) #EBC#Ethiopia#PMAbiyAhmed
Hashtags
TGINSIGHT SIMILAR POSTS
Изворен канал @pythonotes · Post #208 · 29 јан.
Ранее мы уже говорили о том, как выполнить какой-либо код перед открытием интерактивной консоли. Расскажу еще один способ! На самом деле, даже запустив интерпретатор в обычном режиме с выполнением скрипта из файла вы можете в любом месте активировать интерактивный режим. Или даже несколько по очереди. За это отвечает модуль code. Как это может пригодиться? 🔸 Вам не хватает pdb и хочется больше "власти" 🔸 Нужно запросить у юзера данные в достаточно сложном виде. В этом случае можно попросить его создать что ему надо и сохранить в определённую переменную, с которой потом и работать. 🔸 Нужна изолированная среда для выполнения каких-либо действий. 🔸 Просто забавы ради😁 Запускается консоль очень просто import code ic = code.InteractiveConsole() try: ic.interact() except SystemExit: pass Выход обратно на предыдущий уровень происходит как обычно, вызов функции exit() или клавиши Ctrl+D(Ctrl+Z для Windows). Я набросал простой пример с некоторым функционалом 🔹 Меняются символы приглашения 🔹 В неймспейсы добавляются дополнительные объекты 🔹 Считается время, проведённое в интерактивном режиме 🔹 Скрипт просит юзера заполнить переменную и по выходу распечатывает её значение Код здесь ↗️ Для запуска сохраните код в файл и запускайте как обычный скрипт. python my_console.py Для быстрого запуска можно сделать отдельный алиас alias py="python3 /home/username/my_console.py" #tricks#source
Пребарај: #pmabiyahmed
@ebcnewsnow · Post #54156 · 30.04.2026 г., 17:42
"ኢትዮጵያ ለእኛ በምናብ የምትሣል ሕልም ብቻ ሳትሆን በተግባር የምትገነባ እውነታ ናት።" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) #EBC#Ethiopia#PMAbiyAhmed
Hashtags
@ebcnewsnow · Post #53896 · 23.04.2026 г., 11:05
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ምን ምን አሳኩ? ************************* ✅ የAI ኢንስቲትዩት መመሥረት፦ ለምርምር እና ለፈጠራ ሥራዎች የሚውል ራሱን የቻለ ዘመናዊ ተቋም ተገንብቷል። ✅ የሀገር በቀል ቋንቋዎች ልማት፦ የተለያዩ ቋንቋዎች በዲጂታል ዓለም ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የትርጉም እና የንግግር AI ቴክኖሎጂዎች በስፋት እየለሙ ነው። ✅ የጤና ዘርፍ አብዮት (ቀድሞ ምርመራ)፦ የጡት ካንሰርን እና የሳንባ በሽታዎችን በAI ምርመራ ቀድሞ ለመለየት የሚያስችሉ መተግበሪያዎች ወደ ሥራ ገብተዋል። ✅ የሰብል ጥበቃ፦ የሰብል በሽታዎችን እና ተባዮችን በAI ቴክኖሎጂ ቀድሞ በመለየት ለምግብ ዋስትና ትልቅ እገዛ እያደረገ ይገኛል። ✅ ዲጂታል ኢትዮጵያ፦ ሀገራችን በዲጂታል ኢኮኖሚ እንድትመራ የሚያስችል ግልጽ ፖሊሲ እና ፍኖተ ካርታ ተቀርጾ ተግባራዊ እየሆነ ነው። ✅ የሥራ ዕድል፦ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በኮዲንግ እና በዳታ ሳይንስ ሥልጠና እንዲያገኙ በማድረግ ኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ ማዕከል የማድረግ ሥራ ተጀምሯል። #EBC#Ethiopia#PMAbiyAhmed
Hashtags
@ebcnewsnow · Post #53892 · 23.04.2026 г., 08:04
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው በአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ (Assembly of the AU) ተሹመዋል #Ethiopia#PMAbiyAhmed#EBC
Hashtags
@ebcnewsnow · Post #53635 · 16.04.2026 г., 15:43
“የጀመርነውን ልማት እንቀጥላለን፤ ግራ ቀኝ ሳንል በትኩረት እና በትብብር መንፈስ የልማት ጉዟችንን እናስቀጥላለን።” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) #EBC#Ethiopia#PMAbiyAhmed
Hashtags
@ebcnewsnow · Post #54104 · 28.04.2026 г., 11:36
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በማህበራዊ ዘርፍ የተመዘገቡ ውጤቶች የሚገመገሙበት የምክክር መድረክ መካሄድ ጀመረ ************* "የማህበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውና በማህበራዊ ዘርፍ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ዐበይት ውጤቶች የሚቀርቡበት የምክክር መድረክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል። ይህ የምክክር መድረክ በተለይም ባለፉት ስምንት ዓመታት በትምህርት፣ በጤና፣ በክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በባህል፣ በኪነ-ጥበብና ስፖርት እንዲሁም በሴቶች እና ማሕበራዊ ጉዳዮች የተመዘገቡ ውጤቶች በስፋት የሚተነተኑበትና ግምገማ የሚደረግበት መሆኑ ተገልጿል። #EthiopianBroadcastingCorporation#PMAbiyAhmed#EBC
@ebcnewsnow · Post #53478 · 14.04.2026 г., 05:55
የኢትዮጵያ የኢንደስትሪ ጉዞ አዲስ ምዕራፍ እየተራመደ ይገኛል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት የሁለት ክፍሎች ቃለምልልስ ኢትዮጵያ የአዲሱ ዘመን የኢንደስትሪ መስፋፋትን እንዴት እየበየነች እንደሆነ አብራርተዋል። የመጀመሪያውን ክፍል ዛሬ ምሽት 2:30 በኢቢሲ የተለያዩ አማራጮች ይጠብቁ። #PMOEthiopia#PMAbiyAhmed#EBC
Hashtags
@ebcnewsnow · Post #53579 · 15.04.2026 г., 18:33
“ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤት ካልሆነች አታድግም ብቻ ሳይሆን ሰፈሩ አይለወጥም፤ ሰፈሩ ሰላም አያገኝም፤ የዓለም ንግድም ይስተጓጎላል።” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) #EBC#Ethiopia#PMAbiyAhmed#SeaAccess
@ebcnewsnow · Post #53575 · 15.04.2026 г., 18:08
“ኢትዮጵያን የባሕር በር አልቦ አድርጎ መቀጠል በየትኛውም ዘመን አዋጭ አይደለም” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) #EBC#Ethiopia#PMAbiyAhmed#SeaAccess
@ebcnewsnow · Post #53541 · 14.04.2026 г., 18:36
የባሕር በር ደኅንነት ጉዳይ ከምንጊዜውም በላይ አንገብጋቢ ሆኗል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ******************* የዓለም የንግድ እና የኢንዱስትሪ ትሥሥር በአየር፣ በየብስ እና በባሕር ሎጂስቲክስ ስጋቶች ውስጥ መውደቁን ተከትሎ የባሕር በር ደኅንነት ጉዳይ ከምንጊዜውም በላይ አንገብጋቢ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት፣ መንግሥት ከዓመታት በፊት የባሕር ላይ እንቅስቃሴ አደጋ ሊገጥመው እንደሚችል በመተንበይ "ከባሕር ከራቅን 130 ሚሊዮን ሕዝብ አደጋ ውስጥ ይወድቃል" የሚል የጸና አቋም ሲያራምድ ቆይቷል። ምንም እንኳን በወቅቱ ለዚህ ጉዳይ በቂ ትኩረት ባይሰጠውም፣ አሁን ላይ ግን ሀገራት የንግድ መስመሮችን ለጥቅማቸውም ሆነ ተቀናቃኞቻቸውን ለመጉዳት ሲሉ በከፍተኛ ደረጃ እየተቆጣጠሩት ይገኛሉ። በመሆኑም ከባሕር መራቅም ሆነ በአንድ መስመር ላይ ብቻ ጥገኛ መሆን አዋጭ ባለመሆኑ፣ ኢትዮጵያ ለዚህ የሎጂስቲክስ አለመረጋጋት አስቀድሞ መተንበይን ‘ፕሮአክቲቭ የሆነ መፍትሔ’ መከተሏን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል። #EBC#Ethiopia#PMAbiyAhmed#SeaAccess
@ebcnewsnow · Post #53584 · 15.04.2026 г., 18:59
“ኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ማማ ናት” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) #EBC#Ethiopia#PMAbiyAhmed#greenenergy
@ebcnewsnow · Post #53485 · 14.04.2026 г., 07:02
የሉዓላዊነት ልብ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር የተደረገ ቆይታ - ክፍል 1 ዛሬ ምሽት 2:30 በኢቲቪ ዜና ቻናል እና በኢቢሲ ዶትስትሪም አማራጮቻችን ይጠብቁን! #Ethiopia#EBC#PMAbiyAhmed#sovereignty
@ebcnewsnow · Post #54044 · 26.04.2026 г., 08:14
"ኢንዱስትሪ ለመጀመሪያ ጊዜ ግብርናን ተክቶ ከፍተኛውን የኢኮኖሚ ድርሻ የሚይዝበት መዋቅራዊ ሽግግር በጥቂት ዓመታት ውስጥ የሚፈጸም ይሆናል" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) #EBC#Ethiopia#PMAbiyAhmed#industry