@ebcnewsnow · Post #54046 · 26.04.2026 г., 11:23
አትሌት ትግስት አሰፋ በለንደን ማራቶን ክብረ ወሰን በማሻሻል ለ2ኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች ************* ለ49ኛ ጊዜ በተደረገው የለንደን ማራቶን አትሌት ትግስት አሰፋ በበላይነት ስታጠናቅቅ የገባችበት ሰዓት በሴቶች ብቻ በራሷ ተይዞ የነበረውን የዓለም ክብረወሰን አሻሽላለች። በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ ባለው ማራቶን ትግስት አሰፋ እስከ መጨረሻው እልህ አስጨራሽ ፉክክር በማድረግ የገባችበት 2 ሰዓት 15.41 ደቂቃ አዲስ ክብረ ወሰን ሆኖም ተመዝግቧል። የፓሪስ ኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያ ባለቤቷ ትግስት አሰፋ ባለፈው ዓመት በተደረገው የለንደን ማራቶን በሴቶች ብቻ ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት ናት፡፡ የሁለት ጊዜ የበርሊን ማራቶን አሸናፊዋ አትሌት ትግስት፣ የለንደን ማራቶንን ለ2ኛ ተከታታይ ጊዜ ያሸነፈችበት ሆኗል፡፡ ኬንያውያኑ አትሌቶች ሄለን ኦቢሪ እና ጆይስሊን ጅፕኮስጊ 2ኛ እና3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል፡፡ በአንተነህ ሲሳይ #EBC#londonmarathon
Hashtags