@ebcnewsnow · Post #51844 · 21.02.2026 г., 09:41
የፕሬዚዳንት ኤርዶዋን ጉብኝት የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ አቅም ያረጋገጠ ነው፡- ዓለም አቀፍ ምሁራን ******** የቱርክዬ ፕሬዚዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን በኢትዮጵያ ያደረጉት ታሪካዊ ጉብኝት፤ ኢትዮጵያ ያላትን ዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ እንዲሁም በቀጣናው ያላትን ከፍተኛ ተፈላጊነት በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን ዓለም አቀፍ የፖለቲካ እና የደኅንነት ተንታኞች ገለጹ። የቱርክዬ ቲአርቲ የቴሌቪዥን ጣቢያ "STRAIT TALK" ፕሮግራም ላይ ትንታኔ የሰጡት ምሁራን፣ ጉብኝቱ ለቱርክዬ፣ ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካ ቀንድ ያለውን ሰፊ የጂኦ-ፖለቲካዊ ፋይዳ በዝርዝር ዳስሰዋል። በተለይም የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ በተመለከተ፣ ቱርክዬ ጉዳዩ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ የማስቻል ትልቅ አቅም እንዳላት ተጠቁሟል። የቱርክዬ ብሔራዊ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ መህመት ኦዝካን (ፕ/ር) እንደገለጹት፤ ቱርክዬ የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ አስፈላጊነትን ስለምትገነዘብ ጉዳዩ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ጥረት እያደረገች ትገኛለች። በአዲስ አበባ የሚገኘው የኢንስቲትዩት ፎር ሴኩሪቲ ስተዲስ (ISS) ከፍተኛ ተመራማሪ ሞሰስ ክሪስፐስ ኦኬሎ እና የናይሮቢው የሆርን ኢንተርናሽናል ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ሀሰን ኻኔንጄ ይህንኑ ሀሳብ ያጠናክራሉ። እንደ ምሁራኑ ገለጻ፤ ቱርክዬ ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት እንድትሆን እና በቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስር ማዕቀፍ አማካኝነት በርካታ የባህር በሮችን ማግኘት የምትችልበትን ዕድል የሚደግፍ አካሄድን እየተከተለች ይገኛል። የፕሬዝዳንት ኤርዶዋን ጉብኝት የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ አቅም እያደገ መሆኑን እንደሚያሳይ ተመላክቷል። በጉብኝቱ ወቅት በሁለቱ ሀገራት መካከል በኢነርጂ እና በንግድ ዘርፎች የተፈረሙት ስምምነቶች የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ከማነቃቃት ባለፈ፣ ሀገሪቱ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ቀጣናዊ ተጽዕኖ ፈጣሪነት ይበልጥ የሚያጎሉ መሆናቸው ተገልጿል። በላሉ ኢታላ #EBC#Ethiopia#diplomacy#center
Hashtags