Кликнете за преглед на слики 6 слики ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መጪውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋሩ
*************************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ጠዋት ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች እና ጽሕፈት ቤቱ ለሚያሳድጋቸው ሕጻናት የበዓል ማዕድ አጋርተዋል።
ይህ የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር የተከናወነው መጪውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ እንደሆነ ተገልጿል።
Ethiopian Broadcasting Corporation #Ethiopia#Easter#AbiyAhmedAli
Кликнете за преглед на слики 6 слики "ምቹ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች፣ የተሻሻለ የአካባቢ ውበትን እና ጥራታቸውን የጠበቁ የማህበረሰብ መሰብሰቢያ ስፍራዎች በድሬ" ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
**
የድሬ የኮሪደር ልማት ምቹ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች፣ የተሻሻለ የአካባቢ ውበትን እና ጥራታቸውን የጠበቁ የማህበረሰብ መሰብሰቢያ ስፍራዎች በድሬ እውን እንዲሆኑ ማስቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።
በኮሪደሩ ለከተማዋ ነዋሪዎች ገቢ ለማስገኘት የሚያስችሉ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጂንግ ስቴሽን፣ ሱቆች፣ ካፍቴሪያዎች እንዲሁም ደረጃቸውን የጠበቁ የፓርኪንግ ቦታዎች እንዲካተቱበት መደረጉንም ጠቅላይ ሚንስትሩ ጠቁመዋል።
#EthiopianBroadcastingCorporation#AbiyAhmedAli#EBC#Ethiopia#ድሬ
ኢትዮጵያ እና ቱርክዬ በጋራ ለመፈፀም የተግባቡባቸው የስምምነት አጀንዳዎች እና ነጥቦች
**************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፕሬዚዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን ጋር በብሔራዊ ቤተመንግሥት በሰጡት የጋራ መግለጫ ሁለቱ ሀገራት በጋራ ለመፈፀም የተግባቡባቸውን የስምምነት አጀንዳዎች እና ነጥቦች ዘርዝረዋል።
I. የንግድ እና ኢኮኖሚ ትብብር
✅ የንግድ ልውውጥ መጠን፦ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ልውውጥ ቢያንስ ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ እና ከዚያም በላይ ለማሳደግ ታቅዷል።
✅ የዘርፍ ብዝሃነት (Diversification)፦ የንግድ ግንኙነቱ በተወሰኑ ምርቶች ላይ ብቻ ሳይወሰን የተለያዩ የቢዝነስ ዘርፎችን እንዲያካትት ስምምነት ላይ ተደርሷል።
✅ የቱርክዬ ኢንቨስትመንት፦ ታዋቂ የቱርክዬ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት በማድረግ ለሀገር ውስጥ እና ለጠቅላላው የአፍሪካ ገበያ የሚሆኑ ምርቶችን እንዲያመርቱ እና ኤክስፖርት እንዲያደርጉ ድጋፍ ለማድረግ ተስማምተዋል።
II. የባህር በር እና ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ
✅ ኢትዮጵያ ያቀደችውን የ10.2 በመቶ ዕቅድ ለማሳካት የባህር በር ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል።
✅ ለኢትዮጵያ ዕድገት ማነቆ (bottleneck) የሆነውን የሎጂስቲክስ ችግር ለመፍታት የባህር በር ቁልፍ መሆኑ ታምኖበታል።
✅ ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ የባሕር በር እንድታገኝ ቱርክዬ በዲፕሎማሲው መስኩ የራሷን ጫና በመፍጠር የበኩሏን ሚና እንድትጫወት ከስምምነት ተደርሷል።
III. የፀረ-ሽብር ትግል እና አካባቢያዊ ጉዳዮች
✅ ኢትዮጵያ እና ቱርክዬ በፀረ-ሽብር ትግሉ ዙሪያ በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል።
✅ የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ ቱርክዬ ዘንድሮ የምታዘጋጀውን የኮፕ (COP) ስብሰባ በሚቀጥለው ዓመት ለኢትዮጵያ የምታስረክብ በመሆኑ፣ በዝግጅት ሂደት ውስጥ የልምድ ልውውጥ እና መደጋገፍ ለማድረግ ተስማምተዋል።
IV. ሥልታዊ እና ቀጣናዊ ግንኙነት
✅ አፍሪካ በቀጣይ 20 እና 30 ዓመታት ውስጥ የሚኖራትን ከፍተኛ የኢኮኖሚ ሚና ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ቱርክዬ በአፍሪካ ዕድገት ውስጥ ያላትን የጂኦግራፊያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሚና እንድትወጣ መግባባት ላይ ተደርሷል።
✅ በኢትዮጵያ እና በቱርክዬ መካከል ያለውን ጥንታዊ ግንኙነት በመከባበር እና በመደጋገፍ ላይ ተመሥርቶ ይበልጥ ለማጠናከር መሪዎቹ ቃል ገብተዋል።
#Ethiopia#Turkiye#Diplomacy#AbiyAhmedAli#RecepTayyipErdoğan#EthiopianBroadcastingCorporation#EBC#EBCdotstream
Кликнете за преглед на слики 4 слики "ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ ሰላም እና መረጋጋት ያላት አስፈላጊነት ይበልጥ እያደገ መጥቷል" - ፕሬዚዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን
*********
የቱርክዬ ፕሬዚዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ መስኮች ላስመዘገቡት ስኬት “እንኳን ደስ አለዎት” በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንት ኤርዶዋን ይህን ያሉት ዛሬ በብሔራዊ ቤተመንግሥት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር በመሆን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።
ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የሚገኙት ፕሬዚዳንቱ፥ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የትብብር ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ በርካታ ስምምነቶችን ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
ስምምነቶቹ ባቡርን ጨምሮ የትራንስፖርት መሠረተ ልማት ማስፋፋት፣ የፋብሪካዎች ግንባታ፣ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ዝርጋታ እና የቱሪዝም ልማትን እንደሚያካትቱ አብራርተዋል።
ፕሬዚዳንት ኤርዶዋን ረጅም የሀገረ መንግሥት ታሪክ እና የተረጋጋ አስተዳደር ያላት ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ ሰላም እና መረጋጋት አስፈላጊነቷ ይበልጥ እያደገ መጥቷል ብለዋል።
ቱርክዬ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ምዕተ ዓመታትን ያስቆጠረ ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ ከፍተኛ ትኩረት እንደምትሰጥም አክለዋል።
በላሉ ኢታላ
#Ethiopia#Turkiye#Diplomacy#AbiyAhmedAli#RecepTayyipErdoğan#EthiopianBroadcastingCorporation#EBC#EBCdotstream