@ebcnewsnow · Post #53243 · 10.04.2026 г., 08:36
በኢትዮጵያ ካቶላካዊት ቤተክርስቲያን የስቅለት በዓል እየተከበረ ነው ****************** የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን፣ በልደታ ማርያም ካቴድራል በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች እየተከበረ ይገኛል። በዚሁ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓት ላይ፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሀነእየሱስ ሱራፌል፣ ካህናትና ምዕመናን ተገኝተዋል። በዓሉ የኢየሱስ ክርስቶስን መከራና ስቅለት በማሰብ በጸሎት፣ በስግደት እና በልዩ ልዩ መንፈሳዊ መርሃ ግብሮች እየተከበረ ነው የሚገኘው። በሩት ወርቁ #EBC#Ethiopia#CatholicChurch#GoodFriday#CardinalBerhaneyesus#Religion