@ebcnewsnow · Post #53305 · 11.04.2026 г., 07:02
ታሪካዊው ጉዞ በምስል፦ የ"አርቴሚስ 2" ጠፈርተኞች ወደ ምድር ሲመለሱ የሚያሳዩ የመጀመሪያ ፎቶዎች ************* በጨረቃ ዙሪያ ለ10 ቀናት ያደረጉትን አስደናቂ ጉዞ በስኬት አጠናቀው በፓስፊክ ውቅያኖስ ላይ ያረፉት የናሳ ጠፈርተኞች፣ በአሜሪካ የባሕር ኃይል መርከብ ላይ ሲደርሱ የሚያሳዩ የመጀመሪያ ምስሎችን ናሳ ይፋ አድርጓል። እነዚህ ታሪካዊ ፎቶዎች ጠፈርተኞቹ በሰላም ምድር ሲረግጡ ያለውን ደስታና አቀባበል ያሳያሉ። የሰው ልጅ ዳግም ወደ ጨረቃ ለመመለስ ለጀመረው ጉዞ ስኬት የሆኑትን እነዚህን አስደናቂ ምስሎችን ይመልከቱ:- #ArtemisII#NASA#MoonMission#WelcomeHome#SpaceHistory#NASAPhotos