@borkena · Post #5839 · 24.02.2026 г., 06:49
ኢሕአፓ የፓርቲ አባሉ መታሰሩን ገለፀ። የጋሞ ዞን የኢሕአፓ ሰብሳቢ እና የአርባ ምንጭ ከተማ የትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ፓርላማ እጩ አቶ ሰለሞን ሳዳ በጸጥታ አካላት ታስረው መለቀቃቸውን የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። ፓርቲው በትብብሩ፣ በምርጫ ቦርድ ብርቱ ክትትል ከሰዓታት የአፈና እስር በኋላ መለቀቃቸውን በመግለፅ፣ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን አመስግኗል። አቶ ሰለሞን በሌሊት ታፍነው መውረዳቸውን የገለፀው ኢህአፓ፣ እጩው ያለመከሰስ መብት ያለው መሆኑን የዞኑ ሰብሳቢም እንደሆነ አስታውቋል። የመንግስት ካድሬዎች ራሱን ከእጩነት እንዲያገል ከዚህ በፊት በንብረቶቹ ላይ የማቃጠል አደጋ አድርሰውበት ነበር ተብሏል። የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ-ኢህአፓ እጩዎችን በዚህ መንገድ ማሰር፣ ማስፈራራት ተጠናክሮ መቀጠሉ እንደሚያሳዝነው ገልጿል። ከዚህ በፊት አባላቶቹ በተደጋጋሚ መታሰራቸውን ያስታወቀው ፓርቲው፣ የፓርቲ እጩዎችን እያሰሩ፣ እያስፈራሩ መልቀቅ እና ማሳደድ ጤናማ አይደለም ሲል ተቃውሟል። #Ethiopia#news#EPRP#ዜና#NationalElection#EthiopianPolitics