@ebcnewsnow · Post #53967 · 24.04.2026 г., 16:31
“ሌላ ሀገር የላችሁም፤ በቅን ልብ ለሀገራችሁ ሥሩ” - ኮሚሽነር መላኩ ወልደማርያም ***************** የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከማኅበራዊ ሚዲያ በጎ ተጽዕኖ ፈጣሪ ባለሙያዎች ጋር ተወያይቷል። በውይይቱ ላይ ተገኝተው ገለጻ ያደረጉት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር መላኩ ወልደማሪያም፤ ማኅበራዊ ሚዲያ ለመልካም ነገር በቅን ልብ ከተጠቀምንበት ሀገር የመገንባት ኃይሉ ከፍተኛ ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ ዘመን የተሻገሩ ችግሮችን ለመፍታት ብቸኛው አማራጭ ምክክር መሆኑን ያስገነዘቡት ኮሚሽነሩ፣ “ሌላ ሀገር የላችሁም፤ ከኮሚሽኑ ጋር በመተባባር ለሀገራችሁ ሥሩ” ሲሉ ለማኅበራዊ ሚዲያ በጎ ተጽዕኖ ፈጣሪ ባለሙያዎች መልዕክት አስተላልፈዋል። በመሆኑም ሀገራዊ ምክክሩ በሚያልፍባቸው ምዕራፎች በሀገር ባለቤትነት እና በኃላፊነት ስሜት ለማኅበረሰቡ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል። ከጥቂት ወራት በኋላ በሚደረገው ሀገራዊ ጉባኤ ላይም ከቅድመ ምክክር ጀምሮ ከኮሚሽኑ ጋር በመተባበር የዜግነት ኃላፊነታችሁን መወጣት አለባችሁ ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል። በመድረኩ እስካሁን በኮሚሽኑ የተሠሩ ሥራዎችን እና ኮሚሽኑ ከማኅበራዊ ሚዲያ ባለሙያኑዎች የሚጠብቀውን ሥራ በተመለከተ በኮሚሽ ከፍተኛ ባለሙያዎች ገለጻ ተደርጓል። በመድረኩ የተሳተፉ ባለሙያዎች ያሏቸውን ጥያቄዎች አቅርበው በኮሚሽነር መላኩ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል፤ ተሳታፊዎቹ ከኮሚሽኑ ጋር በጋራ እንደሚሠሩም ማረጋገጣቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። #EBC#Ethiopia#Nationaldialogue#socialmedia#socialmediainfluencers