@ebcnewsnow · Post #52861 · 29.03.2026 г., 15:32
ኢጎር ቱዶር ከቶተንሀም ሆትስፐር ጋር ተለያዩ ************** ክሮሺያዊው አሠልጣኝ በቶተንሀም ቤት አንድም የፕሪሚር ሊግ ጨዋታ ሳያሸንፉ በጋራ ስምምነት ተለያይተዋል። የቀድሞው የጁቬንቱስ አሠልጣኝ ካደረጓቸው አምስት የሊግ ጨዋታዎች አቻ የተለያዩት ከሊቭፑል ጋር ብቻ ሲሆን በአራቱ ጨዋታዎች ደግሞ ተሸንፈዋል። ክለቡ ይፋ እንዳደረገው ከሆነ ረዳቶቻቸውም አብረው የለቀቁ ባለሙያዎች ናቸው። ቶማስ ፍራንክን መተካት ክለቡን ከገባበት የውጤት ቀውስ ለማውጣት የተሾመት ሰው በ39ኛ ቀናቸው ተሸኝተዋል። በአንተነህ ሲሳይ #EBC#Sport#PremierLeague#football#TottenhamHotspur