@ebcnewsnow · Post #53685 · 17.04.2026 г., 14:31
ኢትዮጵያ እየተገነባች ነው፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ************** ዛሬ በዓይነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀውን የኢትዮጵያ የመሠረተ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሳምንት በደማቅ ሥነ ሥርዓት ከፍተናል። መሠረተ ልማት ለሀገር ዕድገት ወሳኝ ግብአቶችን በማመላለስ የኢኮኖሚያችን የደም ሥር፣ የብልጽግናችን መሠረት ነው። በዐውደ ርዕዩ የተመለከትነውም ወሳኝ የልማት ተቋሞቻችን፣ መሠረተ ልማትን እንደ ሀገር በቅንጅትና በትብብር የመምራት አዲስ የሥራ ባህል እየገነቡ መሆናቸውን ነው። ባለፉት ዓመታት ፈጠራን፣ ፍጥነትን እና ጥራትን የጉዟችን መርሕ አድርገን በመሥራት ተጨባጭ ስኬቶችን አስመዝግበናል። የመንገድ ርዝመታችንን በብዙ ኪሎ ሜትሮች አሳድገናል፤ ታዳሽ ኃይል የማመንጨት ዐቅማችንን ወደ 10 ሺህ ሜጋ ዋት አካባቢ አድርሰናል። በዲጂታል ዘርፍም የሞባይል ተጠቃሚዎችን 97 ሚልዮን እና የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን ቁጥር 57 ሚልዮን አድርሰናል። በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች የኮሪደር ልማት ሥራዎቻችን "ከተባበርን የማይቻል የለም" የሚለውን መርሐችንን በተግባር ያሳዩ፣ ፍጥነትና ጥራትን ያስተሣሠሩ ፕሮጀክቶች ናቸው። ጉዟችንን ለማጣጣል ለሚሞክሩም ሆነ የውጤቱ ባለቤት እኛ ነን" ለሚሉ ሁሉ መልሳችን አንድ ነው፤ እውነታውንና ፍርዱን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ትተን፣ ሥራችንን እንቀጥላለን! https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0gifZyviBDxs3gC1n26Q6xQYoSWVu3nJLiYuDiYLQ7XewrHh3bCVQ4nDAGHP8j7iwl Ethiopian Broadcasting Corporation #Ethiopia#EBC