TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← Python Заметки

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

Најди сличен содржај

Изворен канал @pythonotes · Post #383 · 28 окт.

Что нового добавили в REPL в Python 3.13 На самом деле серьезно его прокачали! ▫️Както я писал, что для выхода из REPL приходится писать exit, еще и скобки для вызова. И было бы удобней сделать это по аналогии с обычным терминалом. Видимо, я не один такой😁 В новом REPL добавили несколько команд: exit или quit: для выхода. Именно так, без вызова функции! clear: для очистки терминала help или F1: для входа в режим справки (q для выхода) ▫️ Автокомплит по TAB аналогичный Linux-терминалу. Одиночный TAB заполняет самое пхожее совпадение, двойной показывает все доступные варианты. Эти варианты фильтруются по мере набора. ▫️ Ранее при вставке многострочного кода с пустыми строками мы получали ошибку IndentationError, теперь это исправили. Хотя, в некоторых терминалах это даже с 3.6 работает нормально, но зависит от конкретной реализации именно терминала а не Python. На винде точно не работает до 3.13. Пример кода для теста в 3.12 и 3.13 class A: def test(self): pass ▫️ История ввода теперь учитывает многосрочные команды.При нажатии стрелки вверх появятся все строки из прошлого многосрочного ввода, по ним даже можно перемещаться и редактировать. По нажатию F2 можно открыть всю историю ввода. ▫️ Колоризация кода для tracebacks и doctest. Также я заметил что имеет цвет промт функции input(). Кстати, для тестов на винде без установки можно использовать портейбл версию из проектаWinPython. #release

Hashtags

Резултати

Пронајдени 6 слични објави

Пребарај: #londonmarathon

当前筛选 #londonmarathon清除筛选

አትሌት ትግስት አሰፋ በለንደን ማራቶን ክብረ ወሰን በማሻሻል ለ2ኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች ************* ለ49ኛ ጊዜ በተደረገው የለንደን ማራቶን አትሌት ትግስት አሰፋ በበላይነት ስታጠናቅቅ የገባችበት ሰዓት በሴቶች ብቻ በራሷ ተይዞ የነበረውን የዓለም ክብረወሰን አሻሽላለች። በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ ባለው ማራቶን ትግስት አሰፋ እስከ መጨረሻው እልህ አስጨራሽ ፉክክር በማድረግ የገባችበት 2 ሰዓት 15.41 ደቂቃ አዲስ ክብረ ወሰን ሆኖም ተመዝግቧል። የፓሪስ ኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያ ባለቤቷ ትግስት አሰፋ ባለፈው ዓመት በተደረገው የለንደን ማራቶን በሴቶች ብቻ ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት ናት፡፡ የሁለት ጊዜ የበርሊን ማራቶን አሸናፊዋ አትሌት ትግስት፣ የለንደን ማራቶንን ለ2ኛ ተከታታይ ጊዜ ያሸነፈችበት ሆኗል፡፡ ኬንያውያኑ አትሌቶች ሄለን ኦቢሪ እና ጆይስሊን ጅፕኮስጊ 2ኛ እና3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል፡፡ በአንተነህ ሲሳይ #EBC#londonmarathon

አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ ማራቶንን ከ2 ሰዓት በታች የገባ የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሆነ *************** በለንደን ማራቶን ለመጀመርያ ጊዜ የተወዳደረው አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ ማራቶንን ከ2 ሰዓት በታች መግባት የቻለ የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሆኗል። በታሪኩ በማራቶን ለመጀመርያ ጊዜ የተወዳዳረው ዮሚፍ ቀጀልቻ 2ኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ የገባበት 1 ሰዓት 59.41 ደቂቃ የኢትዮጵያ አዲስ ክብረ ወሰን ሆኖ ተመዝግቧል ኬንያዊው አትሌት ሰባስቲያን ሳዌ ውድድሩን በበላይነት ሲያጠናቅቅ የገባበት ሰዓት አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ሆኗል። የባለፈው ዓመት የለንደን ማራቶን አሸናፊው ሰባስቲያን ሳዌ 1 ሰዓት 59.30 ደቂቃ ርቀቱን ለማጠናቀቅ የወሰደበት ሰዓት ሆኗል። የ30 ዓመቱ አትሌት ከሦስት ዓመት በፊት በሀገሩ ልጅ ኬልቪን ኪፕቱም ተይዞ የነበረውን የ2 ሰዓት 00.35 ደቂቃ ክብረ ወሰን በመስበር አዲስ ታሪክ ሠርቷል። በአንተነህ ሲሳይ #EBC#londonmarathon#marathon

አትሌት ሰባስቲያን ሳዌ የማራቶን ሪከርዱ የመኪናው ታርጋ እንዲሆን ተወሰነለት ************* ባለፈው እሑድ በተካሄደው የለንደን ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰንን በመስበር ከሁለት ሰዓት በታች መግባት የቻለው አትሌት ሰባስቲያን ሳዌ፣ ሀገሩ ኬንያ ሲመለስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። ለ49ኛ ጊዜ በተካሄደው የለንደን ማራቶን 1 ሰዓት 59 ደቂቃ ከ30 ሰከንድ በመግባት አዲስ ታሪክ የጻፈው ሰባስቲያን ሳዌ፣ ናይሮቢ ጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በአይነቱ ልዩ የሆነ አቀባበል ተደርጎለታል። አትሌቱን በናይሮቢ ስቴት ሐውስ (ቤተ መንግሥት) ተቀብለው ያነጋገሩት ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ፣ ለተመዘገበው ድንቅ ውጤት ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት አበርክተውለታል። ፕሬዚዳንቱ አትሌቱ የዓለም ክብረ ወሰን በመስበሩ 5 ሚሊዮን እንዲሁም የለንደን ማራቶንን በማሸነፉ 3 ሚሊዮን፣ በአጠቃላይ የ8 ሚሊዮን የኬንያ ሽልንግ ሽልማት ሰጥተውታል። ከገንዘብ ሽልማቱ በተጨማሪም አትሌቱ የፈለገውን መኪና እንዲመርጥ እና የመኪናው የታርጋ ቁጥርም ታሪክ በሰራበት ሰዓት እንዲሰየም ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። በዚህም መሠረት የመኪናው ታርጋ “1:59:30” ተብሎ እንዲጻፍ ይሆናል። ፕሬዚዳንት ሩቶ ይህ አጋጣሚ በሕይወት ዘመን አንድ ጊዜ ብቻ የሚከሰት ብርቅዬ ስኬት መሆኑን ገልጸው ሳዌን አሞካሽተዋል። በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ ባለው የለንደን ማራቶን፣ አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻም በተመሳሳይ ከሁለት ሰዓት በታች በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል። በአንተነህ ሲሳይ #EBC#Ethiopia#marathon#londonmarathon#record

“ወጣት አትሌቶቻችን የታላላቅ አትሌቶቻችንን ፈለግ ተከትለው ለድል ሲበቁ በማየቴ ደስተኛ ነኝ” - ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ *********************** ወጣት እና አስደናቂ ስሉ የገለጿቸው የሀገራችን አትሌቶች የአንጋፋ እና ታላላቅ አትሌቶቻችንን ፈለግ ተከትለው ለድል ሲበቁ መመልከታቸው ታላቅ የደስታ ስሜት እንደፈጠረባቸው ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴ ገለጹ። ፕሬዚዳንቱ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት፣ በለንደን ማራቶን ድንቅ ገድል ለፈጸሙት አትሌት ትዕግሥት አሰፋ እና አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ ያላቸውን አድናቆት ገልጸው፣ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ፕሬዚዳንቱ መልዕክታቸውን ሲቋጩም፣ "የአትሌቶቻችን ድል ይቀጥላል!" ብለዋል። በለንደን ማራቶን አትሌት ትዕግሥት አሰፋ የራሷን የሴቶች ብቻ የዓለም ማራቶን ሪከርድ በ2፡15፡41 በሆነ ሰዓት በድጋሚ ማሻሻሏ እና ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የለንደን ማራቶን አሸናፊ መሆኗ እጅግ አስደናቂ ነው። በተመሳሳይ በወንዶች ዘንድ ዮሚፍ ቀጄልቻ በማራቶን የመጀመሪያ ተሳትፎው ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች በ1፡59፡41 በመግባት ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀበት ውጤት ታሪካዊ ነው። በዚህም ዮሚፍ እና የውድድሩ አሸናፊ የሆነው ኬንያዊው ሰባስቲያን ሳዌ (1፡59፡30) በማንኛውም ይፋዊ ውድድር ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች በመሮጥ የመጀመሪያዎቹ አትሌቶች በመሆን ስማቸውን በዓለም አትሌቲክስ ታሪክ መዝግበዋል። #EBC#londonmarathon#athletics#sport#marathon