@ebcnewsnow · Post #51920 · 25.02.2026 г., 12:27
ከዓድዋ እስከ ሕዳሴ፤ ከሕዳሴ እስከ ባሕር በር! ********************** ዓድዋ ለእኛ ተራራን የመናድ፣ የማይቻለውን የመቻል እና የአንድነት ትልቅ ማህተማችን ነው። ያ ትናንት በዓድዋ ተራራዎች ላይ የነደደው የድል መንፈስ፣ ዛሬም በደምስራችን ውስጥ አለ! ትናንት፦ በዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ፋና ሆንን። ዛሬ፦ ያው የማይበገረው የዓድዋ መንፈስ ታላቁን የሕዳሴ ግድባችንን ዳር አደረሰ። በስንዴ ሉዓላዊነት ታሪክ ተሠራ፤ የዓባይን ወንዝ ለብርሃን እና ለብልፅግና አዋልነው። ነገ፦ ቀጣዩ የታሪክ ምዕራፍ ተጀምሯል፤ የባሕር በር ጉዳይ የሕልውናችን፣ የኢኮኖሚ ነፃነታችን እና የትውልድ ጥያቄ ነው። ትናንት በጋራ ቆመን ያላሸነፍነው ፈተና የለም፤ ዛሬም በዚያው በዓድዋ ፅናት እና በሕዳሴው ወኔ የባሕር በር ጥያቄያችንን በድል እንደምናጠናቅቅ ጥርጥር የለውም! ታሪክ ይደገማል! ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነት ከፍ ብላ ትቀጥላለች! #Ethiopia#AdwaSpirit#GERD#SeaAccess#የሕዳሴግድብ#የባሕርበር#EBC