@ebcnewsnow · Post #51691 · 14.02.2026 г., 16:55
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለባርቤዶስ አቻቸው ሚያ ሞተሊ የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት አስተላለፉ **************** ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞተሊ ለሦስተኛ ጊዜ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመመረጣቸው እንኳን ደስ አለዎት በማለት የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመልዕክታቸው፣ የባርቤዶስ ሕዝብ ላደረገው ስኬታማ የዴሞክራሲ ልምምድ አድናቆታቸውን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሞትሊ ለባርቤዶስ ሕዝብ ዕድገት፣ ብልጽግና እና ዘላቂ ልማት ለሚያደርጉት ጥረት መልካም ዕድል እንዲገጥማቸውም ተመኝተዋል። “በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለውን ጠንካራ ትሥሥር እና ትብብራችንን ለማጠናከር በጋራ እንሠራለን” ሲሉም ገልጸዋል። #EBC#ebcdotstream#Ethiopia#Barbados#Diplomacy