@ebcnewsnow · Post #51758 · 18.02.2026 г., 14:45
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተጨማሪ 8 ወራት የሥራ ጊዜ ተሰጠው ******************* የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተጨማሪ 8 ወራት የሥራ ጊዜ እንዲሰጠው የሕዝብ ተወካዮች ሞክር ቤት ወሰነ። ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የኮሚሽኑን የአራት ዓመታት የሥራ ሪፖርት አድምጧል። ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት የካቲት 14 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ጥሩ ሥራ መሥራቱ ተጠቅሷል። የተሰጠው ጊዜ የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም የሚያበቃ በመሆኑ በትግራይ ክልል አጀንዳ ማሰባሰብ እና የምክክር ጉባዔውን ለማካሄድ ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው በምክር ቤቱ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጠይቋል። ምክር ቤቱም ከየካቲት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የሚቆጠር ተጨማሪ 8 ወራት የሥራ ጊዜ እንዲሰጠው በሙሉ ድምፅ ወስኗል። በባዬ ሙላት #Ethiopia#NationalDialogue#HoPR
Hashtags