TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← Linuxgram 🐧

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

Sib kontenut simili

Kanal tas-sors @linuxgram · Post #17841 · Fra 19

📰 AI Helped Uncover A "50-80x Improvement" For Linux's IO_uring Linux block maintainer and IO_uring lead developer Jens Axboe recently was debugging some slowdowns in the AHCI/SCSI code with IO_uring usage. When turning to Claude AI to help in sorting through the issue, patches were devised that can deliver up to a "literally yield a 50-80x improvement on the io_uring side for idle systems." The code is on its way to the Linux kernel... 🔗 Source: https://www.phoronix.com/news/AI-50-80x-IO-uring #linux#kernel

Riżultati

1 post simili nstab

Tfittxija: #90thyear

当前筛选 #90thyear清除筛选
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #51253 · 23/01/2026 20:30

ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነው አንጋፋ ተቋም *************** 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በማክበር ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለምዕተ ዓመት በተጠጋ ጉዞው የሀገርን ሉዓላዊነት ከማስከበር ባለፈ ለአፍሪካ ሀገራት የአየር ኃይል ምስረታ ያበረከተው ታሪካዊ አስተዋጽኦ በኩራት የሚታወስ ነው። በተለይም በ1960ዎቹ አጋማሽ አፍሪካውያን ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ለመውጣት በሚታገሉበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለአህጉሪቱ ቀዳሚው እና ብቸኛው የሥልጠና ማዕከል ሆኖ ማገልገሉ የምንኮራበት የታሪካችን አንድ አካል ነው። በወቅቱ የአየር ኃይል ለማቋቋም ፍላጎት የነበራቸው ናይጄሪያ፣ ታንዛኒያ እና ኡጋንዳ የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች እና ቴክኒሻኖቻቸውን በአፍሪካ የተደራጀ ዘመናዊ አየር ኃይል ወደ ነበራት ወደ ኢትዮጵያ በመላክ እንዲሰለጥኑ አድርገዋል። እነዚህ ሰልጣኞችም ወደየመጡበት በመመለስ የየሀገራቸውን አየር ኃይል በአዛዥነትና በባለሙያነት አገልግለዋል። ይህ አበርክቶ ኢትዮጵያ ለ‘ፓን-አፍሪካኒዝም’ ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር ያሳየችበት እና የአፍሪካውያን አለኝታ መሆኗን ያስመሰከረችበት ሕያው ታሪክ ነው። በዋሲሁን ተስፋዬ #EBCDotstream#Ethiopia#AirForce#90thyear#anniversary#PanAfricanism