TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← Linuxgram 🐧

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

Sib kontenut simili

Kanal tas-sors @linuxgram · Post #17841 · Fra 19

📰 AI Helped Uncover A "50-80x Improvement" For Linux's IO_uring Linux block maintainer and IO_uring lead developer Jens Axboe recently was debugging some slowdowns in the AHCI/SCSI code with IO_uring usage. When turning to Claude AI to help in sorting through the issue, patches were devised that can deliver up to a "literally yield a 50-80x improvement on the io_uring side for idle systems." The code is on its way to the Linux kernel... 🔗 Source: https://www.phoronix.com/news/AI-50-80x-IO-uring #linux#kernel

Riżultati

5 postijiet simili nstabu

Tfittxija: #goodfriday

当前筛选 #goodfriday清除筛选
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #53271 · 10/04/2026 10:17

የስቅለት በዓል በወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ እየተከበረ ነው ************** የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በአምስት ኪሎ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በልዩ ልዩ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች እየተከበረ ይገኛል። በመርሐ ግብሩ ላይ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ድነት ሲል በመስቀል ላይ የከፈለው መከራና መስዋዕትነት በስፋት ተነስቷል። ይህ በመስቀል ላይ የተፈጸመው ተግባር ሰውን ከኃጢአት ባርነት ነጻ እንዳወጣው ሁሉ፣ የዛሬው ትውልድም ከጥላቻና ከቂም በቀል ባርነት ነጻ መውጣት እንዳለበት ተገልጿል። የመስቀሉ ፍቅር የክፋት ሁሉ ማክተሚያ፣ የይቅርታና የትሕትና ትምህርት መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን፤ አማኙም ይህን ታላቅ መሠረት በመከተል ባለፈ ታሪክ ላይ ከመቆዘም ይልቅ ለነገው ብሩህ ተስፋ ይቅርታን ስንቅ ሊያደርግ እንደሚገባ መልዕክት ተላልፏል። በቤተ ክርስቲያኒቱ በተዘጋጀው በዚህ አገልግሎት ላይ የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎች፣ አገልጋዮች፣ ምዕመናን እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋል። በዕድሉ ፈቀደ #EthiopianBroadcastingCorporation#Ethiopia#GoodFriday#MekaneYesus#AddisAbaba

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #53288 · 10/04/2026 12:25

የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ****************** የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል። በዚህ ታላቅ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሀነእየሱስ ሱራፌል፣ ካህናትና ምዕመናን የተገኙበትን መንፈሳዊ ድባብና የበዓሉን አከባበር የሚያሳዩ ምስሎችን ይመልከቱ። 📸፦ በዮሴፍ እሸቴ Ethiopian Broadcasting Corporation #GoodFriday#CatholicChurchEthiopia#HolyWeek#Ethiopia

Google Facts™ [ ️@googlefactss🌎]

@googlefactss · Post #40895 · 03/04/2026 16:38

In Spain, Good Friday is part of Semana Santa (Holy Week). Cities hold large religious processions. Groups called brotherhoods organize these events. People wear long robes and pointed hoods. They walk slowly as an act of penance. Huge floats called “pasos” show scenes from the crucifixion of Jesus. These can weigh over a ton and are carried by teams underneath. Some cities have music with drums and bands. Others stay completely silent. People also sing emotional songs from balconies. In Seville, processions can last all night. In Málaga, there is a tradition of pardoning a prisoner. In Valladolid, old sculptures from the 16th and 17th centuries are used. Traditional foods include torrijas and buñuelos. 🇪🇸🕯️🎭🥁 [Read more 1] [Read more 2] @googlefactss #GoodFriday#SemanaSanta#Spain#Traditions#History#Culture

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #53278 · 10/04/2026 11:51

የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን እየተከበረ ነው ***************** የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል፡፡ በዓሉ የኢየሱስ ክርስቶስን መከራና ስቅለት በማሰብ በጸሎት፣ በስግደት እንዲሁም የሕመማት ሳምንትን በሚዘክሩ ልዩ ልዩ መንፈሳዊ መርኃ ግብሮች ነው እየተከበረ የሚገኘው። በዕለቱ ቀኑን የሚያወሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የሚነበቡ ሲሆን፤ በዕለተ ስቅለት የተከናወኑ ተግባራት እየታሰበም የስግደት ስርዓት ይከናወናል። #EthiopianBroadcastingCorporation#Ethiopia#Orthodox#GoodFriday#Religion#Prayer

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #53243 · 10/04/2026 08:36

በኢትዮጵያ ካቶላካዊት ቤተክርስቲያን የስቅለት በዓል እየተከበረ ነው ****************** የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን፣ በልደታ ማርያም ካቴድራል በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች እየተከበረ ይገኛል። በዚሁ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓት ላይ፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሀነእየሱስ ሱራፌል፣ ካህናትና ምዕመናን ተገኝተዋል። በዓሉ የኢየሱስ ክርስቶስን መከራና ስቅለት በማሰብ በጸሎት፣ በስግደት እና በልዩ ልዩ መንፈሳዊ መርሃ ግብሮች እየተከበረ ነው የሚገኘው። በሩት ወርቁ #EBC#Ethiopia#CatholicChurch#GoodFriday#CardinalBerhaneyesus#Religion