TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) avatar

TGINSIGHT POST

Post #53301

@ebcnewsnow

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

Weergaven7,550Weergaven van post
Geplaatst10 apr10-04-2026, 20:09
Inhoud

Postinhoud

የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ለታሪካዊው የሰላም ድርድር ወደ ፓኪስታን አመሩ ************************* የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ በአሜሪካ-እስራኤል እና በኢራን መካከል ያለውን ጦርነት ለማቆም በሚደረገው ድርድር ላይ ለመሳተፍ ወደ ፓኪስታን፣ ኢስላማባድ አቅንተዋል። ቫንስ ወደ ፓኪስታን ከመነሳታቸው በፊት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ ከኢራን ጋር የሚደረገው ድርድር “ውጤታማ ይሆናል” የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል። ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለድርድሩ ግልጽ መመሪያ እንደሰጧቸው የጠቀሱት ቫንስ፣ “ኢራን በቅን ልቦና ለመደራደር ዝግጁ ከሆነች እኛም እጃችንን ለመዘርጋት ዝግጁ ነን” ብለዋል። ሆኖም ኢራን ድርድሩን ለተንኮል ወይም ጊዜ ለመግዛት የምትጠቀምበት ከሆነ የአሜሪካ የልዑካን ቡድን እንደማይቀበለው አስጠንቅቀዋል። በኢራን የፓርላማ አፈ-ጉባኤ መሀመድ ባገር ጋሊባፍ እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አባስ አራቅቺ የተመራው የሀገሪቱ የልዑካን ቡድንም ኢስላማባድ መግባቱ ተዘግቧል። ድርድሩ ፊት ለፊት ወይስ በአደራዳሪዎች አማካኝነት ይካሄድ እስካሁን በይፋ አልተገለጸም። የድርድሩ ዋና ዓላማ ወዲያውኑ ስምምነት ላይ መድረስ ባይሆንም፣ ለዘላቂ ሰላም የሚረዱ የጋራ ነጥቦች ላይ መግባባትና ንግግሩ እንዲቀጥል ማድረግ ነው። የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሼህባዝ ሸሪፍ መስተንግዶውን "ለመላው ሙስሊም ዓለም ኩራት ነው" ሲሉ የገለጹት ሲሆን፣ በከተማዋ ከ10 ሺህ በላይ የጸጥታ ኃይሎች ከፍተኛ ጥበቃ እያደረጉ ይገኛሉ። #JDVance#USA#Iran#peace#Pakistan#Islamabad#EBC