TGINSIGHT CHAT
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
@ebcnewsnow
News and mediaEBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1 @ETVkidschannel @EBCWORLD1 @etventertainment1
Recente posts
Pagina 1 van 84 · 1,008 posts
Geplaatst 4 mei
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በ3.3 ቢሊዮን ብር ወጪ በጣና ዳርቻ የሚገነባውን ግዙፍ የሆቴል ፕሮጀክት አስጀመሩ *************************** ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በባሕር ዳር ከተማ፣ በጣና ሐይቅ ዳርቻ የሚገነባውን ግዙፍ እና ዘመናዊ የቱሪዝም መዳረሻ ግንባታ ዛሬ በይፋ አስጀምረዋል። ይህ 4PBS (ፎር ፖይንት ባይ ሸራተን) በሚል ስያሜ የሚገነባው ሆቴል፤ ታሪካዊውን ጣና ሆቴል ዘመኑን በዋጀና ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ዳግም ለመገንባት ያለመ ነው። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በወቅቱ ባደረጉት ንግግር፤ የሚገነባው ግዙፍ ፕሮጀክት የከተማዋን የቱሪዝም ገጽታ ወደ ላቀ ከፍታ የሚያሸጋግርና የሀገሪቱን የብልጽግና ጉዞ የሚያንፀባርቅ መሆኑን ገልጸዋል። ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በተለያዩ የልማት ዘርፎች እያመጣ ያለውን ለውጥ ያደነቁት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህንንም ፕሮጀክት በስኬትና በተቀመጠለት ጊዜ የማጠናቀቅ ኃላፊነት እንዳለበት አሳስበዋል። ለፕሮጀክቱ ግንባታ 3.3 ቢሊዮን ብር በጀት የተያዘ ሲሆን፣ በግንባታው ሂደትም ዘመናዊና ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ግብዓቶች ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ተመላክቷል። በአሸናፊ እንዳለ #EthiopianBroadcastingCorporation#Ethiopia#TourismDevelopment#BahirDar#MidrocInvestmentGroup#LakeTana
Geplaatst 4 mei
የአርበኞች ቀንን ምክንያት በማድረግ 21 ጊዜ መድፍ ይተኮሳል **************** በነገው ዕለት የሚከበረውን 85ኛውን የአርበኞች መታሰቢያ ቀን ምክንያት በማድረግ መድፍ እንደሚተኮስ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። የአርበኞች መታሰቢያ ቀንን ምክንያት በማድረግ ነገ ሚያዝያ 27 ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ 21 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ የመከላከያ ሚኒስቴር ለኢቢሲ በላከው መግለጫ አመልክቷል። Ethiopian Broadcasting Corporation #አርበኞችቀን#መድፍ
Geplaatst 4 mei
አሜሪካ በሆርሙዝ ሰርጥ የንግድ መርከቦችን ለማጀብ ማቀዷን ተከትሎ ኢራን ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ሰጠች ***************** የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሀገራቸው የጦር መርከቦች በሆርሙዝ ሰርጥ የሚያልፉ ገለልተኛ የውጭ ሀገራት የንግድ መርከቦችን የማጀብ እና ደኅንነት የማስጠበቅ ሥራ እንደሚጀምሩ አስታውቀዋል። ፕሬዝዳንቱ ይህንን ጥረት "ሰብዓዊ ተግባር" ሲሉ የገለጹት ሲሆን፤ ርምጃው የተዘጋውን የውኃ መስመር ለሚያቋርጡ መርከቦች ከለላ ለመስጠት ያለመ መሆኑን አመላክተዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለእስራኤሉ የመገናኛ ብዙኃን ተቋም 'ካን ኒውስ' በሰጡት ቃል፣ ጦርነቱን ለማስቆም በቅርቡ ከኢራን የቀረበውን የሰላም ሀሳብ መርምረው ተቀባይነት የሌለው ሆኖ እንዳገኙት ተናግረዋል። የኢራን ሀሳብ ውድቅ ቢደረግም፤ አሜሪካ ለቴህራኑ የ14 ነጥብ የውሳኔ ሃሳብ ምላሽ የሚሆን አዲስ የተሻሻለ ረቂቅ ስምምነት ማቅረቧ...https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid03xtpeFzmmAhRL9r2sCcdXspKRs7CGjzr7nvr2ZPRUCxktynAzq18C571G4q1UTJRl
Geplaatst 4 mei
ሀገር በልጆቿ ጥረትና ትጋት ትገነባለች ፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ ******************* የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ በአራዳ ፓርክ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚቆየውን 16ኛውን ከተማ አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት ዓውደ-ርዕይ በዛሬው ዕለት በይፋ ከፈቱ። ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ባስተላለፉት መልዕክት፤ “የቴክኖሎጂ ልህቀት ለሀገር ብልጽግና!” በሚል መሪ ሀሳብ ለ16ኛ ጊዜ በምናካሂደው በዚህ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት፣ የብልፅግና ተምሳሌት የሆነችው ከተማችን አዲስ አበባ በዘርፉ ያላትን ተወዳዳሪነት በተግባር የምናሳይበት ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በቴክኖሎጂ ፈጠራና ሽግግር የዓለምን ፈጣን ዕድገት መቀላቀል መቻሏን ያነሱት ከንቲባ አዳነች፣ ቀደም ሲል ተኪ ምርቶችን ባለማምረትና በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት ይገጥሙ የነበሩ የዕድገት ውስንነቶች አሁን ላይ በትላልቅ ስኬቶች እየተቀረፉ መሆናቸውን...https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02Y7uppJ1WQBhE9F7Z1ajnSGYACAYhUuKQGyQXyh91Ys5sGWpWUWvLYeskCSAaV6dCl
Geplaatst 4 mei
ማስታወቂያ አሁንም የሂሳብ ቁጥር ይጠይቃሉ? ረጅም ቁጥሮችን ከመጻፍ፣ ደጋግሞ ከማረጋገጥ እና ከመሳሳት ስጋትን የሚገላግልዎትን የእኛን QR ኮድ ‘Scan’ በማድረግ ክፍያዎን በሰከንዶች ውስጥ ይፈጽሙ! Ammas Lakkoofsa Herregaa Gaafachaa Jirtuu? Lakkoofsa dheeraa barreessuu, irra deebi’anii mirkaneessuu fi yaaddoo dogoggoraa kan isin baraaru Koodii QR keenya ‘Scan’ gochuun kaffaltii keessan sekondiiwwan keessatti xumuraadha! #Coopbank#SmartQR#ScanToPay#DigitalPayments#CashlessLife#PaySmart
Geplaatst 4 mei
103 አዲስ የገጠር ከተሞች እና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ********************* የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዘጠኝ ወራት ውስጥ 103 አዳዲስ የገጠር ከተሞች እና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ማድረጉን አስታወቀ። ተቋሙ ፍትሃዊ የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ባከናወነው ዘርፈ-ብዙ ተግባር ከዋናው ግሪድ እና ከግሪድ ውጪ ባሉ አማራጮች በርካታ አካባቢዎችን ማዳረስ መቻሉን አገልግሎቱ ለኢቢሲ ዶትስትሪም በላከው መረጃ አመላክቷል። የአገልግሎቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ጌቱ ገረመው እንደገለጹት፣ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ኃይል ካገኙት አካባቢዎች መካከል 82ቱ ከዋናው የኤሌክትሪክ መረብ (ግሪድ) ጋር የተገናኙ ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ 21 የገጠር ከተሞችና መንደሮች ደግሞ በፀሐይ ኃይል አማራጭ (ኦፍግሪድ)...https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02AJVcFytuP47BT2i4rksuz6QgijzBrK4BfMYFT4XPD7eXxLh4fgqkQVN1H4pAwfNdl
Geplaatst 4 mei
ማስታወቂያ የገንዘብ እጥረት ሲያጋጥምዎ ከእጅ ስልክዎ የጎደልዎትን የሚሞሉበት የችግር ጊዜ ዋስትናዎ የሆነው የሲንቄ ባንክ ወቢ ዲጂታል የብድር አገልግሎትን በመጠቀም አስቸኳይ የገንዘብ ፍላጎትዎን ያሟሉ፡፡ #Siinqee_Bank#Baankii_Siinqee#ሲንቄ_ባንክ#Siinqee_Digital#Siinqee_Ihsan#Financial_Inclusion#EMPOWERED_TOGETHER
Geplaatst 4 mei
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2026 የAPEX መንገደኞች ምርጫ 'በአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ' ሽልማትን አሸነፈ ******** ኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2026 የAPEX መንገደኞች ምርጫ 'በአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ' (Best Airline in Africa) ሽልማትን አሸነፈ። ይህ ሽልማት አየር መንገዱ የተሳለጠ፣ ምቹ እና አስተማማኝ አገልግሎት ለደንበኞቹ ለማቅረብ ያለውን ያልተቋረጠ ትጋት ከማሳየቱ ባሻገር በአቪዬሽን አገልግሎት ዘርፉ ያለውን መሪነት...https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid024J7aYhvwikXZyCcm2r48JZGBywFnmq1w8PuVeLNVxM2ycPeKN7EZChZYjtU8Jvf3l
Geplaatst 4 mei
ምክክር ለዘላቂ ሰላም፤ የጎዴ የሀገር ሽማግሌዎች ቁርጠኝነት ************** በሸበሌ ዞን የጎዴ ከተማ የሀገር ሽማግሌዎች በሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ልዩነቶችን በውይይት ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የድርሻቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ። በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ እየተከናወነ ባለው በዚህ ሂደት ላይ ንቁ ተሳትፎ እንደሚያደርጉ የሀገር ሽማግሌዎቹ አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እያከናወነ ያለው ተግባር ሰላማዊ የመፍትሔ ባህልን የሚያጠናክር መሆኑን የሀገር ሽማግሌ ሱልጣን ቃሊብ ሱልጣን ድእስ አብዲ አስረድተዋል። የሀገር ሽማግሌ ሱልጣን አሊ አብዲ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ ሰላም እንዲጸና እና ብሔራዊ መግባባት እንዲጎለብት ኮሚሽኑ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራት...https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0u5kP3pNbNNigCEdarPAmGWcCFH93uKWhSSHnxwa1PvrbZqjqhUfF1cJjNvCuuJ61l
Geplaatst 4 mei
የዘንድሮው “ኢትዮጵያ ታምርት” ኤክስፖን ለየት የሚያደርገው ምንድን ነው? ********************** ከመላው የሀገሪቱ ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ ከ186 በላይ ኢንዱስትሪዎች፤ አዳዲስ ዘርፎች የታከሉበት። ቀደም ሲል ከተከናወኑት ኤክስፖዎች ይበልጥ የገዘፈ፣ የሰፋ እና የደመቀ!
Geplaatst 3 mei
"ኢትዮጵያ ግዙፍ የሴራሚክስ ፋብሪካዎችን በቅርቡ ታስመርቃለች" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ******************** ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ኢትዮጵያ በኮንስትራክሽን ግብዓቶች ራሷን ለመቻል የምታደርገው ጥረት ውጤት እያሳየ መሆኑን ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ኢትዮጵያ ታምርት" ኤክስፖ 2018 መርቀው በከፈቱበት ወቅት እንደተናገሩት፣ በቅርቡ ከአንድም ሁለት ግዙፍ የሴራሚክስ ፋብሪካዎች ይመረቃሉ ብለዋል። እነዚህ ፋብሪካዎች የሀገራችንን የሴራሚክስ ፍላጎት መቶ በመቶ የመመለስ አቅም እንዳላቸውም አረጋግጠዋል። ኢትዮጵያ ላለፉት በርካታ ዓመታት የወደብ አገልግሎት እና ጠንካራ ሎጂስቲክስ በሌለበት ሁኔታ ለኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚውሉ ድንጋዮችን ከውጭ ስታስመጣ መቆየቷን አስታውሰዋል። "ከእንግዲህ ድንጋይ መሸከም የለብንም፤ የሴራሚክስ አምራቾቻችንን ወደ ፖርሲሊን፣ ግራናይት እና ማርብል ምርት ማሳደግ አለብን" ሲሉ አቅጣጫ አስቀምጠዋል። ለሙሉ መረጃው ... https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02g7WRPPDhVKXt7xSkY67u91zEeD3a7V2tx7Q29xpLD6uHiZ3t2CLt8uJX75yt3t8il
Geplaatst 3 mei
ማንችስተር ዩናይትድ ሊቨርፑልን 3 ለ 2 አሸነፈ **** በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 35ኛ ሳምንት ማንችስተር ዩናይትድ ሊቨርፑልን 3 ለ 2 በማሸነፍ ነጥቡን ወደ 64 ከፍ አድርጓል። በኦልድ ትራፎርድ በተደረገው ጨዋታ ማቲያስ ኩኛ፣ ቤንጃሚን ሼሽኮ እና ኮቢ ማይኖ የማንችስተር ዩናይትድን ግቦች አስቆጥረዋል። ቤንጃሚን ቬሽኮ በውድድር ዓመቱ በሊጉ 11ኛ ግቡን ነው ማስቆጠር የቻለው። ዶሚኒክ ሶቦዝላይ እና ኮዲ ጋክፖ የሊቨርፑልን ግቦች ያሰቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው። ሊቨርፑል የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎውን የሚያረጋግጥበትን አጋጣሚ ሳይጠቀምበት ቀርቷል። #EthiopiaBroadcastingCorporation
Hashtags