TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
Inhoud
Postinhoud
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ውስጥ ከኢራን ጋር ድርድር ሊኖር እንደሚችል ፍንጭ ሰጡ ****************** የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚደረገው ሁለተኛው ዙር ድርድር በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ውስጥ በፓኪስታን ሊካሄድ እንደሚችል መናገራቸውን ኒው ዮርክ ፖስት ዘግቧል። ፕሬዚዳንቱ ዛሬ ለጋዜጣው በስልክ በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ “በእውነቱ እዚያው ኢስላማባድ ብትቆዩ ይሻላል፤ ምክንያቱም በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ውስጥ አንድ ነገር ሊከሰት ይችላል፤ እኛም ወደዚያ የመሄድ ዝንባሌ አለን” ብለዋል። ይህ አስተያየት የተሰጠው ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የተካሄደው የመጀመሪያው ዙር ድርድር ያለስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ ነው። ፕሬዚዳንት ትራምፕ ቀደም ሲል ሁለተኛው ዙር ቀጥተኛ ድርድር በአውሮፓ ውስጥ የሆነ ቦታ ሊካሄድ እንደሚችል ጠቁመው ነበር። ሆኖም ኒው ዮርክ ፖስት እንደዘገበው፣ ፕሬዚዳንቱ ቆየት ብለው በድጋሚ በደወሉበት ወቅት ድርድሩ ወደ ኢስላማባድ የመመለስ ዕድሉ "ከፍተኛ" መሆኑን ገልጸዋል። በዚሁ ንግግራቸውም የፓኪስታኑን የጦር አዛዥ አሲም ሙኒርን "ጥሩ ሥራ እየሠሩ ነው" ሲሉ አድንቀዋል። #EBC#world#middleeast#iran#usa#peacetalks