TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) avatar

TGINSIGHT POST

Post #53548

@ebcnewsnow

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

Weergaven8,000Weergaven van post
Geplaatst15 apr15-04-2026, 08:55
Inhoud

Postinhoud

"ኢራን የኑክሌር ጦር መሣሪያ ፍላጎቷን ከተወች፣ በኢኮኖሚ እንድትበለጽግ እናደርጋለን" - አሜሪካ ***************** በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለው ውጥረት ባለበት ሁኔታ፣ የምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ አዲስ መግለጫ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕም የሰላም ንግግሩ በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ውስጥ ሊቀጥል እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተዋል። በፓኪስታን የተደረገው የመጀመሪያ ዙር ንግግር ያለምንም ስምምነት ቢጠናቀቅም፣ ቫንስ አሁን ስላለው ሂደት "ጥሩ ስሜት ይሰማኛል" ብለዋል። በሀገራቱ መካከል ያለው ጥልቅ አለመተማመን በአንድ ጀንበር እንደማይፈታም አክለዋል። ትራምፕ የሚፈልጉት ተራ ስምምነት ሳይሆን ለውጥ የሚያመጣ ትልቅ ስምምነት ስለመሆኑ ቫንስ ገልጸዋል። ትራምፕ፣ "ኢራን የኑክሌር ጦር መሣሪያ የማምረት ሐሳቧን ከተወች፣ ኢራን እንድትበለጽግና የዓለም ኢኮኖሚ አካል እንድትሆን እናደርጋለን" ብለዋል። ለአሜሪካ የ"ብልጽግና" ግብዣ ኢራን የምትሰጠው ምላሽ በጉጉት እየተጠበቀ ነው። በሌላ በኩል ካናዳ፣ እንግሊዝ፣ አውስትራሊያ እና ሌሎች 7 ሀገራት በሊባኖስ ያለው ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆም በጋራ መግለጫ ጠይቀዋል። ከሦስቱ ሀገራት በተጨማሪ መግለጫውን ብራዚል፣ ኮሎምቢያ ኢንዶኔዥያ፣ ጃፓን፣ ዮርዳኖስ፣ ሴራሊዮን እና ስዊዘርላንድ ፈርመውታል። ሀገራቱ በሊባኖስ እየተባባሰ ባለው የሰብዓዊ ቀውስ እና የተፈናቃዮች ቁጥር መጨመር ከፍተኛ ስጋት እንዳላቸው ገልጸዋል። በተለይም ባለፈው መጋቢት ወር ሦስት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰላም አስከባሪዎች መገደላቸውን አውግዘዋል። #MiddleEast#Iran#USA#negotiation#Trump#Vance#Lebanon