ሲፒጄበእስር ላይ የሚገኙጋዜጠኞች ፍትሐዊ እና ግልጽ የፍርድ ሂደት እንዲያገኙ አሳሰበ። አለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (ሲፒጄ)፣ በሽብርተኝነት ወንጀል የተከሰሱ አራት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ፍትሐዊ፣ ግልጽ እና ሕጋዊ ሥርዓቱን የጠበቀ የፍርድ ሂደት እንዲያገኙ ጠይቋል። ድርጅቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ፣ መስከረም አበራ፣ ገነት አስማማው እና ዳዊት በጋሻው አስፈላጊው የሕግ ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ጠቁሟል። ድርጅቱ እነዚህ ጋዜጠኞች በአማራ ክልል ከነበረው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ በሰሩት ዘገባ ምክንያት በቁጥጥር ስር ውለው ላለፉት ሦስት ዓመታት ገደማ በእስር ላይ እንደሚገኙ የጠቆመው ሲፒጄ፣ ጋዜጠኞቹ ለረጅም ጊዜ በእስር መቆየታቸው እና የቀረበባቸው ክስ ክብደት በኢትዮጵያ ያለውን የፕሬስ ነፃነትን አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን አስጠንቅቋል። በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግስት ዓለም አቀፍ የፍትሐዊ የፍርድ ሂደት መስፈርቶችን እንዲያከብር ጠይቋል። የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቅርቡ በሰጠው ብይን፣ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበው ማስረጃ ተከሳሾቹን ለመከላከል የሚያበቃ ነው በማለቱ፣ ጋዜጠኞቹ በመጪው ግንቦት ወር መከላከያቸውን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። #Ethiopia#EthiopianMedia#EthiopianJournalist#CPJ#news#ዜና
TGTGInsightаналитика telegramLIVE / telegram public index
TGINSIGHT SIMILAR POSTS
Найти похожее
Источник @vfplotnikov · Post #1663 · 29 апр.
Актриса ЛАРИСА УДОВИЧЕНКО родилась 29 апреля 1955 года в Вене (Австрия). Подробнее: https://zen.yandex.ru/media/id/5e0e2740028d6800ad2e198e/glazami-fotografa-plotnikova-larisa-udovichenko-rodilas-29-aprelia-6054449b53791e021b279558 #Удовиченко#29апреля#Плотников
Hashtags
Результаты
Найдено 1 похожих постов
Поиск: #ethiopianmedia
当前筛选 #ethiopianmedia清除筛选