TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← Find Blog👁发现博客

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

查找相似内容

Source channel @FindBlog · Post #643 · 3月1日

Flare Stack Blog ——基于 Cloudflare Workers 的现代化全栈博客 CMS ## 核心功能 • 文章管理 — 富文本编辑器,支持代码高亮、图片上传、草稿/发布流程 • 标签系统 — 灵活的文章分类 • 评论系统 — 支持嵌套回复、邮件通知、审核机制 • 友情链接 — 用户申请、管理员审核、邮件通知 • 全文搜索 — 基于 Orama 的高性能搜索 • 媒体库 — R2 对象存储,图片管理与优化 • 用户认证 — GitHub OAuth 登录,权限控制 • 数据统计 — Umami 集成,访问分析与热门文章 • AI 辅助 — Cloudflare Workers AI 集成 • 主题系统 — 可扩展的主题模板,支持完整替换所有页面和布局 • 导入导出 — 支持Markdown导入导出,保留图片以及Frontmatter Flare Stack Blog 的所有面向用户的页面与布局均通过 主题契约(Theme Contract) 与业务逻辑解耦。你可以在不修改任何路由或数据逻辑的前提下,完整替换博客的视觉表现层。 项目地址:https://github.com/du2333/flare-stack-blog #Platform#Cloudflare 频道:@FindBlog 群组:@FindBlog_Group

Results

找到 73 条相似帖子

搜索 #ebcdotstream

当前筛选 #ebcdotstream清除筛选
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #53588 · 2026/04/16 03:50

"ምንም ጥርጥር የለውም፤ ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ዐሥር ዓመታት በአፍሪካ ውስጥ አውራ ሀገር ትሆናለች" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) Ethiopian Broadcasting Corporation #Ethiopia#ebcdotstream

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #53310 · 2026/04/11 07:37

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት ************ የአፍሪኤግዚም ባንክ ፕሬዝደንት የሆኑትን ዶክተር ጆርጅ ኢሎምቢን ዛሬ ተቀብያለሁ። በነበረን የጋራ ቆይታ፣ ስትራቴጂካዊ ግንኙነታችንን በምናጠናክርባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገናል። #EBC#ebcdotstream#Ethiopia

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #52443 · 2026/03/18 02:59

"በከተሞቻችን እንደ ውኃ፣ መብራት፣ የፍሳሽ መሠረተ ልማት፣ ጤና እና ትምህርት መሠረታዊ ፍላጎቶችን በጥራት ማቅረብ የመደመር መንግሥት አንዱ ግብ ነው። የከተሞች ጸጥታና ደኅንነት ከዕድገታቸው እና ከግባቸው ጋር መመጣጠን አለበት። በተጨማሪም የከተሞች ክፍሎች የንግድ አካባቢ፣ የመኖሪያ አካባቢ እና የመኖሪያ አካባቢ ተብለው ተለይተው መገንባት አለባቸው። ይህም መሠረተ ልማትን፣ አገልግሎትን እና የሕዝብ ፍላጎትን ያሣልጣል።" የመደመር አንቀፅ ገፅ 237 #EBC#Ethiopia#EBCDOTSTREAM

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #51260 · 2026/01/25 07:38

ባንኮች ለተመረጡ የገቢ ዕቃዎች የጉምሩክ ዋጋን እንደ አመላካች ዋጋ እንዲጠቀሙ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ ************************ ባንኮች ለተመረጡ የገቢ ዕቃዎች የብድር ሰነድ (Letters of Credit) ይሁን ሌላ ክፍያ መንገድ ሲፈቅዱ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ተመንን እንደ አመላካች ዋጋ እንዲጠቀሙ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሐምሌ 2016 ዓ.ም ተግባራዊ ያደረገውን የውጭ ምንዛሪ መመሪያን ተከትሎ፣ የሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን በገበያ እንዲወሰን መደረጉ ይታወቃል። መመሪያው ባንኮች ከደንበኞቻቸው ጋር በመደራደር የውጭ ምንዛሪ መሸጫ እና መግዣ ተመኖችን መወሰን እንዲችሉ ይፈቅዳል። በተጨማሪም ባንኮች ቀደም ሲል ይጠቀሙበት የነበረው ዝቅተኛ የገቢ ዕቃዎች ዋጋ መመሪያ (Minimum Price Directive) በመሰረዙ፤ አሁን ግን በአዲሱ የውጭ ምንዛሪ መመሪያ መሠረት የገቢ የዕቃዎችን ዋጋ ትክክለኝነት የማረጋገጥ ኃላፊነት አለባቸው። ይሁን እንጂ፣ ባንኮች ለብድር ሰነድ (Letters of Credit) የሚጠቀሙባቸው ዋጋዎች ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የማጣቀሻ ዋጋዎች ጋር ሲነፃፀሩ ከፍተኛ ልዩነት እንዳላቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባደረገው ክትትል አረጋግጧል። በመሆኑም የዋጋ ልዩነቶቹን ለማስተካከልና የዋጋ ማጣቀሻዎችን ለማጣጣም ሁሉም ባንኮች ከጥር 19 ቀን 2018 ዓ.ም (January 27, 2026) ጀምሮ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ተመንን እንደ አመላካች ዋጋ ይጠቀማሉ። ይህም በባንክ ሥርዓቱ እና በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን መካከል ያለውን የዋጋ ልዩነት ለማስወገድ እና የውጭ ምንዛሪ መረጃዎችን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። #EBC#ebcdotstream#Ethiopia

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #51788 · 2026/02/19 08:39

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሁለተኛው ክርክር በኢቢሲ በቅርብ ቀን ይጠብቁን! ብልጽግና ፓርቲ አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) እናት ፓርቲ ሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት ፓርቲ በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ የተደረገ ሁለተኛው የምርጫ ክርክር በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን። በምርጫ ብቻ!! #ethiopianbroadcastingcorporation#EBCDOTSTREAM

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #51614 · 2026/02/12 17:11

የምርጫ 2018 የፖለቲካ ፓርቲዎች የመጀመርያ ክርክር በኢቢሲ በቅርብ ቀን ይጠብቁን! ብልጽግና ኢዜማ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ነፃነትና እኩልነት በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ የተደረገ የመጀመሪያ የምርጫ ክርክር በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን። በምርጫ ብቻ!! #ethiopianbroadcastingcorporation #EBCDOTSTREAM

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #51565 · 2026/02/09 16:59

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሰው አልባ ፖሊስ አገልግሎት በይፋ አስጀመሩ ************** ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሰው አልባ ፖሊስ አገልግሎት ወይም ስማርት ፖሊስ አገልግሎት በይፋ አስጀምረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው፤ ዛሬ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሰው አልባ ፖሊስ አገልግሎት ወይም ስማርት ፖሊስ አገልግሎት አስጀምረናል ብለዋል። ‎ይህ አገልግሎት ዜጎች የፖሊስ አገልግሎትን በተሻለ ፍጥነት እና በቴክኖሎጂ ታግዘው እንዲያገኙ እንደሚያስችል ገልፀዋል። በተጨማሪም አገልግሎቱ ለፖሊስ ፈጣን እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችለው እና የወንጀል መከላከል ስራውን የሚያቀላጥፍ መሆኑን ጠቅሰዋል። የዚህ አገልግሎት መጀመር በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የህግ አስከባሪ አካላት ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የተጀመረው የሪፎርም ስራን ውጤታማነት የሚያሳድግ ይሆናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልእክታቸው። #EthiopianBroadcastingCorporation#Ebcdotstream#Ethiopia

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #51212 · 2026/01/23 13:44

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአየር ኃይል 90ኛ ዓመት የአቪዬሽን ኤክስፖን ጎበኙ ***************** ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የኢፌዲሪ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት ክብረ በዓልን ምክንያት በማድረግ በተሰናዳው የአቪዬሽን ኤክስፖ 2026 ይፋዊ የመክፈቻ መርሃግብር ላይ ተገኝተዋል። ‎ኤክስፖው “የወደፊቱን የአቬሽን አቅም በጋራ እንገባ” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ሲሆን ኢትዮጵያ ለአቪዬሽን እና ኤሮስፔስ ልማት፣ አለም አቀፍ ትብብርን በማጠናከር እና ሀገራችንን በአቪዬሽን ልማት የቀጣናው እና አኅጉሩ የፈጠራ፣ የክህሎት ልማት እና የዘላቂ እድገት ማዕከል ማድረግ ላይ ያላትን ጽኑ አቋም እና ተግባር ያሳያል። #PMOEthiopia#EBC#ebcdotstream

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #51543 · 2026/02/08 12:49

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ የኮሪደር ልማት ሥራ ላይ እየተሳተፉ ለሚገኙ ሰራተኞች ማዕድ አጋሩ ***************** ዛሬ በ24/7 የሥራ ባሕል የከተማችንን የኮሪደር ልማት ሥራዎች እያፋጠኑ ከሚገኙ ታታሪ ሰራተኞች ጋር ማዕድ በማጋራት አበረታተናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡ ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ እነዚህ ብርቱ ሰራተኞች በተለያዩ የግንባታ ሳይቶች፤ በተለይም በካዛንቺስ የሕፃናት ዓለም፣ በስፖርት ፓርክ እና በአዲስ አኳሪየም ግንባታዎች፣ እንዲሁም ከኡራኤል እስከ ቦሌ ቪ.አይ.ፒ፣ ከኢንግሊዝ ኢምባሲ 22 እስከ ቦሌ ፍሬንድሺፕ ሆቴል እና ከውኃ ልማት እስከ ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ እየተከናወኑ ባሉ መጠነ ሰፊ የኮሪደር ልማት አያያዥ መስመሮች ላይ ሌት ተቀን የሚተጉ ናቸው ብለዋል። በከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜት ለከተማችን ሁለንተናዊ ዕድገት በእውቀታቸውና በጉልበታቸው እያበረከቱ ላለው አስተዋፅኦ ከልብ እናመሰግናለን፤ አዲስ አበባ ሁልጊዜም ታመሰግናችኋለች ሲሉም ገልፀዋል። በከተማችሁ መልማት በመደሰት ሁሌ በማዕድ ማጋራት እና እነዚህን ብርቱ ሰራተኞ በማበረታት መርኃ ግብር እየተሳተፋችሁ ላላችሁ ባለሀብቶች በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል ከንቲባዋ በመልእክታቸው። #EthiopianBroadcastingCorporation#Ebcdotstream#Ethiopia#AddisAbaba

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #51848 · 2026/02/21 18:12

የኮሪደር ልማት ስራዎች በርካታ ከተሞችን እየለወጡ ይገኛሉ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ****************** ‌‎የኮሪደር ልማት ስራዎች የተሻለ ሀገርን ለትውልድ የመገንባት አካል ሆነው በርካታ ከተሞችን እየለወጡ ይገኛሉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፤ በሐዋሳ ከተማ በሁለተኛው ምዕራፍ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎችን በዛሬው ዕለት ተመልክተናል ብለዋል። የኮሪደር ልማት ስራዎች የተሻለ ሀገርን ለትውልድ የመገንባት አካል ሆነው በርካታ ከተሞችን እየለወጡ ይገኛሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አጠቃላይ ስራዎቹ እያደገ ለመጣው ከተሜነት ሀገርን ያዘጋጁ መሆናቸውንም ገልፀዋል። #EthiopianBroadcastingCorporation#Ebcdotstream#Ethiopia#PMAbiy

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #51684 · 2026/02/14 11:44

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ቦካይ ጋር መከሩ ***************** ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ቦካይ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ ከላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ቦካይ ጋር ተገናኝተን በቴክኖሎጂ፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና በተለይም ኢትዮጵያ ለመመስረት ባቀደችው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ በተመለከተ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገናል ብለዋል። #EthiopianBroadcastingCorporation#Ebcdotstream#Ethiopia#PMAbiy

123•••67
上一页第 1/7 页下一页