TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← GitHub 红队武器库🚨

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

查找相似内容

Source channel @githubredteam · Post #82821 · 5月4日

🚨 GitHub 监控消息提醒 🚨发现关键词:#EXP#CVE 📦项目名称:SacveExperience 👤项目作者:epaliza-design 🛠开发语言: None ⭐Star数量: 0 | 🍴Fork数量: 0 📅更新时间: 2026-05-04 23:00:19 📝项目描述: El Primer Simposio Argentino de Cardiología Veterinaria reúne a los referentes más destacados para impulsar la formación continua, la interdisciplina y el desarrollo de la especialidad en Argentina y la región. 🔗点击访问项目地址

Hashtags

Results

找到 4 条相似帖子

搜索 #gamozone

当前筛选 #gamozone清除筛选
Borkena

@borkena · Post #6006 · 2026/03/13 18:05

የ3 ቀናት ብሔራዊ ሀዘን ታወጀ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተው የመሬት ናዳ እና የጎርፍ አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የ3 ቀናት ብሔራዊ ሀዘን ታውጇል፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፥ በዞኑ ጋጫ ባባ ወረዳ ላካ ቀበሌ መጋቢት 2 ቀን 2018 ዓ.ም በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት ከጠፉ 125 ሰዎች ውስጥ የ80 ወገኖችን ሕይወት ማለፉን ገልፀዋል። የቀሪ ሰዎች አስከሬን ፍለጋ ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ ምክር ቤቱ በዜጎቻችን ላይ በተከሰተው አደጋ ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶታል ብለዋል። በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፕብሊክ የሰንደቅ አላማ አዋጅ ቁጥር 654/2001 አንቀጽ 22 ንዑስ አንቀጽ (2) ብሔራዊ የሀዘን ቀንና ሰንደቅ አላማው ዝቅ ብሎ የሚውለበለብባቸውን ሁኔታዎች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ እንደሚያሳልፍ መደንገጉን ተናግረዋል። በዚሁ መሠረት በመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸው ያለፈው ዜጎቻችንን በማስመልከት ከመጋቢት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ3 ቀናት ብሔራዊ የሀዘን ቀን ታውጇል ብለዋል። በእነዚህ ቀናት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰንደቅ አላማ በሁሉም የሀገሪቱ ግዛቶች፣ በኢትዮጵያ መርከቦች፣ በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እና ቆንጽላ ጽ/ቤት ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ውሳኔ መተላለፉን ገልፀዋል። #Ethiopia#News#gamozone#ዜና#የጎርፍአደጋ#ጋሞዞን#ቦርከና_ዜና

Borkena

@borkena · Post #5985 · 2026/03/12 13:56

በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት የሟቾች ቁጥር 107 ደረሰ። ​በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ፣ ካምባ እና ቦንኬ ወረዳዎች በደረሰ የመሬት መንሸራተትና የጎርፍ አደጋ የ107 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ደምሴ አድማሱ (ዶ/ር) ተናግረዋል። ​ዋና አስተዳዳሪው በአደጋው 127 ሰዎች መጥፋታቸው እና እስካሁን አለመገኘታቸውን ገልፀዋል። በአካባቢው መልከዓ ምድር አስቸጋሪነት ምክንያት አስክሬን ፍለጋው መጓተቱን ተናግረዋል። ለተፈናቀሉ ወገኖች አስቸኳይ የዕለት እርዳታ እየቀረበ መሆኑን ጠቁመዋል። ​​#Ethiopia#gamozone#South_Ethiopia#ዜና#ቦርከና_ዜና#ጋሞዞን#የጎርፍአደጋ

Borkena

@borkena · Post #5968 · 2026/03/10 11:48

እናት ከሁለት ልጆቿ ጋር በመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸው አለፈ። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ቦንኬ ወረዳ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የአንድ ቤተሰብ የሆኑ እናትና ሁለት ልጆች ሕይወታቸውን አጥተዋል። አባወራው ከፍተኛ ጉዳት ተደርሶባቸው በቦንኬ ጋዜሶ ጤና ጣቢያ ህክምና እየተደረገላቸው ነው ተብሏል። ከአርባ ምንጭ–ጊና–ቦንኬ የሚያገናኘው ዋና መንገድ በመሬት መንሸራተት ተዘግቶ በመገኘቱ ተጎጂውን ወደ ሆስፒታል ለማድረስ ችግር መፍጠሩ ተገልጿል። ዞኑ በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳና በከምባ ዙሪያ ወረዳ አካባቢዎች የጎርፍ ስጋት መኖሩን የጋሞ ዞን ፖሊስ አስጠንቅቋል፤ ነዋሪዎችም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪውን አቅርቧል። ​ #Ethiopia#Borkena_news#Ethiopiannews#gamozone#አርባምንጭ#ጋሞዞን#ዜና#ቦርከና_ዜና