አባ ሳዊሮስ በአርሲ በደረሰው የምዕመናን ግድያ ሀዘናቸውን ገለፁ። የሀዘን መግለጫ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሽርካ ወረዳ በጃዊ ቀበሌ 21 ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂዎች ሕይወታቸው ማለፉን ተከትሎ የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን እንገልጻለን። በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሽርካ ወረዳ በጃዊ ቀበሌ በታጣቂዎች ጥቃት የካቲት 19 ለ 20 አጥቢያ አንድ ካህን፣ ሁለት ሴቶች እና 18 ወንድ ኦርቶዶክሳውያን በግፍ መገደላቸውን የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ለጽሕፈት ቤታችን ከጻፉት ደብዳቤ ስንመለከት እጅግ በከፍተኛ ኀዘን ተሰምቶናል። በመሆኑም በሀገረ ስብከቱ በተለያዩ ጊዜያት በኦርቶዶክሳዊያን ልጆቻችን ላይ የሚፈጸመውና የተፈጸመው ዘግናኝና እጅግ አሳዛኝ ግድያዎች የኦርቶዶክሳዊያን ልጆቻችንን በየትኛውም የአገራችን ክፍል በነጻነት የመኖርና ሃይማኖታዊ ሥርዓታቸውን የመፈጸም መብትን የሚጋፋ በመሆኑ የክልሉና የፌዴራል መንግሥታት ጉዳዮን በልዩ ሁኔታ መከታተልና የማያዳግም መፍትሔ የሚያገኝበት መንገድ መፈለግ እንዳለባቸው እያሳሰብን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤትም የአካባቢው ችግር በመሰረቱ እስከሚፈታ ድረስ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እንወዳለን። በመጨረሻም በዚህ ዘግናኝና አሳዛኝ ግድያ ሕይወታቸውን ላጡ ልጆቻችን እግዚአብሔር አምላክ መንግሥተ ሰማያትን እንዲያወርስልን እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸውም መጽናናትን እንዲሰጥልን የቅድስት ቤተክርስቲያናችን የዘወትር ጸሎቷ መሆኑን እንገልጻለን። አባ ሳዊሮስ #Ethiopia#Oromiyaa#ArsiZone#ethiopianorthodoxtewahedochurch#EOTC
🚨 GitHub 监控消息提醒 🚨发现关键词:#漏洞#检测#分析 📦项目名称:Open-Audit 👤项目作者:elegent-administrator 🛠开发语言: Python ⭐Star数量: 0 | 🍴Fork数量: 0 📅更新时间: 2026-05-16 03:56:40 📝项目描述: Open Audit是面向企业研发、开发者群体的AI智能明文代码安全审计工具,基于Python语言开发、FastCGI架构搭建,融合Semgrep工具链与自主研发的AI Agent,精准匹配数字时代代码安全审计的市场核心需求。工具直击行业传统审计工具误报率高、扩展能力弱、无法检测逻辑漏洞三大痛点,通过AI Agent深度分析漏洞代码上下文实现误报过滤,开放标准化接口支持企业自定义扩展漏洞检测方向,依托Agent的逻辑推理能力突破常规工具技术瓶颈,实现逻辑漏洞精准审计,同时完成跨平台适配,为中小微企业、互联网研发团队、个人开发者提供高效、可定制、高精准的代码安全审计解决方案,全方位筑牢代码研发安全防线。 🔗点击访问项目地址
找到 3 条相似帖子
搜索 #eotc
ሲኖዶሱ በአርሲ የደረሰውን ጥቃት አወገዘ። በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ አርሲ የተፈጸመው የንጹሐን ግድያ ለዘመናት የዘለቀውን የሃይማኖቶች ተከባብሮ የመኖር እሴት ለመናድ የታለመ ነው ሲል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ድርጊቱን በጽኑ አውግዟል። በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በተለያዩ ወረዳዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥቃት በአዲስ መልክ ቀጥሎ የ21 ንጹሐን ወገኖች ሕይወት በግፍ ማለፉን ቋሚ ሲኖዶስ በመሪር ኃዘን ገልጿል። ኦርቶዶክሳውያን በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል በነፃነት የመኖርና ሥርዓተ አምልኮ የመፈጸም ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸው ሊከበር ይገባል ያለው ቋሚ ሲኖዶሱ፤ የፌዴራልና የክልሉ መንግሥት እርምጃዎች በአፋጣኝ እንዲወስዱ አሳስቧል። በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በተደጋጋሚ እየተፈጸመ ያለው ሞትና መፈናቀልም ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን በየትኛውም የሀገራችን ክፍል በነጻነት ሠርተው የመኖርና ሥርዓተ አምልኮ የመፈጸም ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን የሚጋፋ በመሆኑ የክልሉና የፌዴራል መንግሥት ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ ተከታትለው አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጡበት ቋሚ ሲኖዶስ በጥብቅ ያሳስባል፣እንዲሁም ለተፈጸመው ግፍ አፋጣኝ ፍትሕ እንዲሰጥና ገዳዮች በሕግ እንዲጠየቁ እና የዜጎችን ደኅንነትና ንብረት የማስጠበቅ የመንግሥት ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ፤የሀገር ሰላምና የቤተ ክርስቲያን አንድነት ዐቢይ ኮሚቴ ከመንግሥት ጋር በመነጋገር ዘላቂ መፍትሔ እንዲያመጣ ቋሚ ሲኖዶስ አሳስቧል ። በመጨረሻም ቋሚ ሲኖዶስ ስለስሙ መከራን ለተቀበሉ" ንጹሐን ዕረፍተ ነፍስን፣ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ተመኝቷል። #Ethiopia#AddisAbaba#Oromia#EOTC#Arsi#Ethiopiannews#ዜና#አርሲ
የአእላፋት ዝማሬ በምስል #Genna#aelafatzimare#Mezmur#EOTC#orthodox#church#EBC