TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← () => "翠楼屋"

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

查找相似内容

Source channel @lambdaexpression · Post #206 · 4月20日

前段时间一直被MajdataPlay的外键输入问题困扰:有玩家反映majplay会无征兆地出现拖判和吃音,但是内屏一切正常 因为我是第一次接触游戏开发,IO这方面也完全没经验 一开始我和bb本怀疑是线程调度的问题,即:IO线程时间片被其他线程挤占了,导致IO线程无法及时处理HID设备回报。为了验证这个猜想,我们尝试提高了IO线程的优先级,照旧 接下来我怀疑是我那套框架有问题:majplay是根据上一帧与这一帧的按键状态判断按键是不是"click"。为此我重写了这部分的实现,改进了IO线程与主线程之间的交互,问题照旧....... 到这里我已经怀疑这不是majplay的锅:IO线程没有任何异常,IO线程与主线程的交互没有问题,Note判定逻辑也没有问题,那就是设备确实没有回报给majplay或者设备发过来的回报中按键确实没有按下,但是大佬说hdd没有这种问题.....(人已经快崩溃了,这完全看不透也摸不着,因为我用单片机模拟玩家打高速纵连是完全没有问题的,我在家里用手台测试也没有问题) 到最后,bb本灵光一闪,说有没有可能是led刷新率过高,把按键控制板干爆炸了?我们让大佬把led刷新间隔从16ms改成100ms,吃音问题瞬间没有了,无语了 。。。。。。。。。。。。。。。。。。。。 adx是一个控制板同时管理按键和led,为什么我没有遇到吃音问题呢,因为我的手台不是adx的... #dev

Hashtags

Results

找到 7 条相似帖子

搜索 #ausummit2026

当前筛选 #ausummit2026清除筛选
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #51695 · 2026/02/15 17:27

ኢትዮጵያ እንግዶቿን በክብር እየሸኘች ነው **************** በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤና በ2ኛው የጣሊያን-አፍሪካ ስብሰባ ላይ የተሳተፉ መሪዎች በኢትዮጵያ የነበራቸውን ቆይታ በስኬት ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ ወደ አገራቸው መመለስ ጀምረዋል። መሪዎቹ ከቦሌ ዓለም-አቀፍ አየር ማረፊያ ሲነሱም የክብር አሸኛኘት እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። #EthiopianBroadcastingCorporation#ebcdotstream#Ethiopia#AUSummit2026

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #51583 · 2026/02/11 06:44

ለ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ ከእንግዶች አቀባበል ጋር በተያያዘ ዝግ የሚደረጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ ******************** የጸጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል 39ኛውን የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ አስመልክቶ አጠቃላይ የጸጥታ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱ የሚታወቅ ሲሆን የተሽከርካሪ ፍሰቱን ለማሳለጥና ከእንግዶች አቀባበል ጋር በተያያዘ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል። በዚህም ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ብራስ እንዲሁም ከቦሌ መድኃኒያለም በአትላስ ወደ ቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ በመሪዎቹ ጉባኤ ምክንያት ከዛሬ የካቲት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚደረግ ይሆናል። በተጨማሪም በሌሎች እንግዶች በሚያርፉባቸው ዋና ዋና አደባባዮችና የአጀብ መስመሮች አሽከርካሪዎች ቅድሚያ በመስጠትና የትራፊክ ፖሊስ አባላትን ትዕዛዝ በማክበር የተለመደ ቀና ትብብራቸውን እንዲያደርጉ፤ በተጠቀሱት ቦታዎች ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪዎችን ማቆም የተከለከለ መሆኑንም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙም በነጻ የስልክ መስመሮች 990፣ 991፣ 987፣ 816 እንዲሁም በ011-1-26-43-59፣ 011-5-52-63-02/03፣ 011-5-52-40-77፣ 011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81 እንዲሁም በእጅ ስልኮች የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (Citizen Engagement Application) EFPApp በመጠቀም ጥቆማ መስጠት እንደሚገባም ጥሪ ተላልፏል። #EthiopianBroadcastingCorporation#Ebcdotstream#Ethiopia#AUSummit2026

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #51694 · 2026/02/15 11:14

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአዲሱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር ጋር ተወያዩ ******* አዲሱን የኅብረታችን ሊቀመንበር፤ የቡሩንዲ ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬን አግኝቼ በተረከቡት ኃላፊነት ደስታዬን ገልጬላቸዋለሁ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። የአፍሪካውያን ጠንካራ ትብብር እና ቀጣናዊ ግንኙነቶችን ለማሳደግ በሚያስችሉ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገናል ብለዋል። #EBC#PMAbiy#Ethiopia#AUSummit2026

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #51686 · 2026/02/14 12:30

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቦትስዋና ፕሬዝዳንት ዱማ ቦኮን ጋር ተወያዩ ****************** ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቦትስዋና ፕሬዝዳንት ዱማ ቦኮን ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ የቦትስዋና ፕሬዝዳንት ዱማ ቦኮን አግኝቼ፤ በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች፣ ለተሻለ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ያሉ እድሎች እና አፍሪካን ቀጣይ የሚመራ ትውልድን ማብቃት ላይ በጋራ በምንሰራበት አውድ ዙሪያ ውይይት አድርገናል ብለዋል። #EthiopianBroadcastingCorporation#Ebcdotstream#Ethiopia#PMAbiy#Diplomacy#AUSummit2026

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #51685 · 2026/02/14 12:07

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሊቢያ ፕሬዝዳንታዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር መሃመድ አልመንፊ ጋር ተወያዩ ***************** ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሊቢያ ፕሬዝዳንታዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር መሃመድ አልመንፊ ጋር በቀጣናዊ ልማት እና የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ውይይት ማድረጋቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል። #EthiopianBroadcastingCorporation#Ebcdotstream#Ethiopia#PMAbiy#Diplomacy#AUSummit2026

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #51624 · 2026/02/12 19:46

የተመድ ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አዲስ አበባ ገቡ **************** የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል። ዋና ጸሀፊው ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የፕላንና ልማት ሚኒስተር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል። 39ኛው የኅብረቱ የመሪዎች ጉባዔ "ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፥ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ በመጪው ቅዳሜ እና እሁድ ይካሄዳል። በጉባኤው የሚሳተፉ መሪዎችም ወደ አፍሪካ መዲና አዲስ አበባ በመግባት ላይ ናቸው። በሞላ አለማየሁ #EthiopianBroadcastingCorporation#Ethiopia#UNSG#AntónioGuterres#AUSummit2026

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #51584 · 2026/02/11 07:17

ከጉባኤ አዳራሾች ባሻገር የሚተርክ አዲስ ገጽታ እና የኢትዮጵያ ዓለም አቀፋዊ ዝግጁነት ******************* ኢትዮጵያ 39ኛውን የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ እና 2ኛውን የጣሊያን-አፍሪካ ስብሰባ ለመካፈል ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ ከፍተኛ ልዑካንን ለመቀበል ከመቼውም ጊዜ በላይ ስንዱ መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። መዲናዋ በከፍተኛ ጥራትና በዘመናዊ መልክ የተገነቡ ዓለም አቀፍ የስብሰባ አዳራሾችን እንዲሁም ደረጃቸውን የጠበቁ ምቹ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማሟላት እንግዶቿን ለመቀበል በላቀ ደረጃ መዘጋጀቷን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል። ይህ አዲሱና ማራኪው የከተማዋ ገጽታ የእንግዶችን ቆይታ ልዩና የማይረሳ እንደሚያደርገው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ተሳታፊዎች ከጉባኤው መድረኮች ባሻገር በአፍሪካውያን ጥረት እያደገ የመጣውን አዲሱን የቱሪዝም ዘርፍ እንዲመለከቱና ቆይታቸውን እንዲያራዝሙ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። ይህ ዝግጁነት ኢትዮጵያ ለዲፕሎማሲያዊ ሁነቶች ያላትን ምቹነት የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን፣ አህጉራዊ ትብብርንና የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ ያላትን ቁርጠኝነት ዳግም ያረጋገጠ መሆኑ ተመላክቷል። #Ethiopia#PMAbiyAhmed#AfricanUnion#AUSummit2026#ItalyAfricaSummit#TourismEthiopia#EthiopianBroadcastingCorporation