TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← () => "翠楼屋"

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

查找相似内容

Source channel @lambdaexpression · Post #206 · 4月20日

前段时间一直被MajdataPlay的外键输入问题困扰:有玩家反映majplay会无征兆地出现拖判和吃音,但是内屏一切正常 因为我是第一次接触游戏开发,IO这方面也完全没经验 一开始我和bb本怀疑是线程调度的问题,即:IO线程时间片被其他线程挤占了,导致IO线程无法及时处理HID设备回报。为了验证这个猜想,我们尝试提高了IO线程的优先级,照旧 接下来我怀疑是我那套框架有问题:majplay是根据上一帧与这一帧的按键状态判断按键是不是"click"。为此我重写了这部分的实现,改进了IO线程与主线程之间的交互,问题照旧....... 到这里我已经怀疑这不是majplay的锅:IO线程没有任何异常,IO线程与主线程的交互没有问题,Note判定逻辑也没有问题,那就是设备确实没有回报给majplay或者设备发过来的回报中按键确实没有按下,但是大佬说hdd没有这种问题.....(人已经快崩溃了,这完全看不透也摸不着,因为我用单片机模拟玩家打高速纵连是完全没有问题的,我在家里用手台测试也没有问题) 到最后,bb本灵光一闪,说有没有可能是led刷新率过高,把按键控制板干爆炸了?我们让大佬把led刷新间隔从16ms改成100ms,吃音问题瞬间没有了,无语了 。。。。。。。。。。。。。。。。。。。。 adx是一个控制板同时管理按键和led,为什么我没有遇到吃音问题呢,因为我的手台不是adx的... #dev

Hashtags

Results

找到 5 条相似帖子

搜索 #election2018

当前筛选 #election2018清除筛选
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #51949 · 2026/02/28 06:55

ምርጫ - የነገን ብሩህ ተስፋ ለመቅረጽ የሚያስችል ቁልፍ መሣሪያ ****** ታላቁ የሰላም ተምሳሌት ኔልሰን ማንዴላ "ምርጫ የተሻለች ዓለምን ለመገንባት በእጃችን ያለ ታላቅ ዕድል ነው" የሚል አባባል ነበራቸው። ይህም የምርጫ ድምፃችን ከማንኛውም ቁሳዊ ኃይል ይልቅ የነገን ብሩህ ተስፋ ለመቅረጽ በእጃችን ያለ ዋነኛ ቁልፍ መሣሪያ መሆኑን ያሳያል። መራጭ መሆን መብት ብቻ ሳይሆን ለሀገርና ለሚመጣው ትውልድ የሚደረግ ታላቅ የዜግነት ኃላፊነት ነው። በምንሰጠው ድምፅ ፍትሕን፣ ልማትንና ሰላምን የመገንባት አቅም አለን። የምርጫ ድምፃችን የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ መሠረት ነው። ስለዚህ ታሪክን የዴሞክራሲ ታሪክን በጎ መልኩ ለመገንባት እያንዳንዱ ድምፅ የራሱ የሆነ ክቡር ዋጋ እንዳለው ተገንዝበን፣ በበሰለና በኃላፊነት ስሜት መሳተፍ ይገባል። ምርጫ የግለሰቦች ውድድር ሳይሆን የጋራ ቤታችንን የምናድስበት የጋራ ራዕያችን ነው! እኔ የምርጫ ጉዳይ ያገባኛል፣ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እሳተፋለሁ! እርስዎስ? በጌትነት ተስፋማርያም #EBC#Election2018#Ethiopia

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #51889 · 2026/02/23 06:31

ወደ ለምለሙ ምድር ለመሻገር የሁላችንም እጅ ያስፈልጋል ************** ጥንት በአንድ ታላቅ ተራራ ግርጌ የሚኖሩ ሰዎች ወደ ማዶ የሚገኘው ለም ምድር ለመሻገር ፈልገዋል። ሆኖም ወደዚያ ለመሻገር የሚያስችል ድልድይ አልነበረም። የሀገሬው ሽማግሌዎችም አንድ ጥበብ ተናገሩ፤ "ጠንካራ ድልድይ መሥራት ይገባል፤ ይህ ድልድይ የሚገነባው እያንዳንዱ ሰው በሚያመጣው ጠጠር ነው" አሉ። እያንዳንዷ እናት፣ እያንዳንዱ ወጣትና አዛውንት አንዲት ጠጠር አመጡ። አንዱ "ጠጠሬ ትንሽ ናት" ብሎ አላቃለለም፤ ሌላውም "እኔ ባላመጣ ምን ይጎድላል?" ብሎ ወደ ኋላ አላለም። በመጨረሻም፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ትናንሽ ጠጠሮች ተከመሩ። እነዚያ ተለይተው ሲታዩ የማይረቡ የሚመስሉ ትናንሽ ጠጠሮች ተገጣጥመው ታላቅና ጽኑ ድልድይ ገነቡ። ሕዝቡም በገዛ እጁ በገነባው ድልድይ ላይ ተራምዶ ወደ ለምለሙ ምድር ተሻገረ። ያ ድልድይ የቆመው በአንድ ሰው ጥንካሬ ሳይሆን፣ በእያንዳንዱ ግለሰብ ተሳትፎና እምነት ነበር። ምርጫ ልክ እንደዚያ ድልድይ ግንባታ ነው። እያንዳንዷ ድምፅ እንደ አንዲት ጠጠር ናት። ጠጠሮቹ ሲደመሩና ሲተባበሩ ማንም የማይበግረው መሠረት ይሆናሉ። የዴሞክራሲው ድልድይ እንዲጸና፣ የነገው ብርሃን እንዲመጣና ለምለሙ ተራራ እንዲደረስበት፤ እጅ ለእጅ ተያይዘን በምርጫ መሳተፍ የዜግነት ግዴታችን ብቻ ሳይሆን የታሪክ አደራችንም ነው። #EBC#election2018#Ethiopia#EthiopianBroadcastingCorporation

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #52601 · 2026/03/22 12:20

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ አሃዞች *********** ከየካቲት 28 - መጋቢት 10/2018 ዓ.ም ጠቅላላ የተመዘገቡ መራጮች፦ ከ18.5 ሚሊዮን በላይ የጾታ ስብጥር፦ ወንዶች፦ 10,133,639 ሴቶች፦ 8,422,698 የምርጫ አስፈጻሚዎች ብዛት፦ 187,028 ባለሙያዎች #Ethiopia#Election2018#Democracy#EthiopianBroadcastingCorporation

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #52129 · 2026/03/06 16:37

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የእጩዎች ዝርዝር ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ይፋ ይደረጋል - ምርጫ ቦርድ ********************* የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚወዳደሩ እጩዎች ዝርዝር ከዛሬ ምሽት ጀምሮ በየምርጫ ክልሎቹ ይፋ እንደሚደረግ አስታውቋል። የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ እንደገለጹት፤ ቦርዱ በፖለቲካ ፓርቲዎች የቀረቡለትን የእጩዎች ዝርዝርና ተያያዥ ሰነዶችን በጥንቃቄ የመመርመር ሥራውን አጠናቋል። በዚህ የምርጫ ሒደት 47 ፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሳተፉ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 10 ሺህ 934 እጩዎች ለምርጫ ቀርበዋል። ከእነዚህም መካከል 2 ሺህ 198 እጩዎች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ 8 ሺህ 736 እጩዎች ደግሞ ለክልል ምክር ቤቶች የሚወዳደሩ ናቸው። በምዝገባው ሂደት 73 የግል እጩዎች የተካተቱ ሲሆን፣ ከጠቅላላው የእጩዎች ቁጥር ውስጥ 2 ሺህ 760 ሴቶችና 8 ሺህ 174 ወንዶች መሆናቸውን ቦርዱ ገልጿል። በሳምሶን ገድሉ #EBC#Ethiopia#Election2018#NEBE#Democracy#Candidates#ኢትዮጵያ#ምርጫ2018

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #52008 · 2026/03/03 12:45

ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ የሚከናወንባቸው ሦስት ዘመናዊ አማራጮች ***************** ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚከናወነው የመራጮች ምዝገባ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ባገናዘበ መልኩ በሦስት ዋና ዋና አማራጮች እንደሚከናወን ቦርዱ አስታውቋል። የመጀመሪያው አማራጭ መራጮች በተለመደው አሠራር በአካል በምርጫ ጣቢያ በመገኘት ምዝገባ የሚያከናውኑበት መደበኛ ሂደት ነው። ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምዝገባ ሂደቱን ይበልጥ ቀልጣፋ ለማድረግ 'ምርጫዬ' የተሰኘ አዲስ የሞባይል መተግበሪያ በቅርቡ ተደራሽ ያደርጋል። መራጮች ይህንን መተግበሪያ ከፕሌይ ስቶር (Play Store) ወይም ከአፕ ስቶር (App Store) በማውረድ ባሉበት ሆነው ራሳቸውን መመዝገብ የሚችሉ ሲሆን፥ ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀውን የዌብ አማራጭ ሊንክም በቦርዱ ድረ-ገጽ ላይ ማግኘት ይቻላል። ሦስተኛው አማራጭ ደግሞ በምርጫ ጣቢያዎች በሚገኙ የምርጫ አስፈጻሚዎች እገዛ በታብሌት (Tablet) የሚከናወን የዲጂታል ምዝገባ ሂደት መሆኑ ተገልጿል። በምርጫ ጣቢያም ሆነ በግል ስልክ የሚከናወኑት የዲጂታል ምዝገባ አማራጮች ተፈጻሚ የሚሆኑት ቦርዱ የኢንተርኔት ተደራሽነትን መሠረት በማድረግ ይፋ በሚያደርጋቸው የተወሰኑ አካባቢዎች ላይ ብቻ መሆኑ ታውቋል። በቦርዱ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የመራጮች ምዝገባ ከየካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ይጀመራል። #Ethiopia#Election2018#DigitalRegistration#NEBE#EthiopianElection#NewsUpdate