TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← () => "翠楼屋"

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

查找相似内容

Source channel @lambdaexpression · Post #206 · 4月20日

前段时间一直被MajdataPlay的外键输入问题困扰:有玩家反映majplay会无征兆地出现拖判和吃音,但是内屏一切正常 因为我是第一次接触游戏开发,IO这方面也完全没经验 一开始我和bb本怀疑是线程调度的问题,即:IO线程时间片被其他线程挤占了,导致IO线程无法及时处理HID设备回报。为了验证这个猜想,我们尝试提高了IO线程的优先级,照旧 接下来我怀疑是我那套框架有问题:majplay是根据上一帧与这一帧的按键状态判断按键是不是"click"。为此我重写了这部分的实现,改进了IO线程与主线程之间的交互,问题照旧....... 到这里我已经怀疑这不是majplay的锅:IO线程没有任何异常,IO线程与主线程的交互没有问题,Note判定逻辑也没有问题,那就是设备确实没有回报给majplay或者设备发过来的回报中按键确实没有按下,但是大佬说hdd没有这种问题.....(人已经快崩溃了,这完全看不透也摸不着,因为我用单片机模拟玩家打高速纵连是完全没有问题的,我在家里用手台测试也没有问题) 到最后,bb本灵光一闪,说有没有可能是led刷新率过高,把按键控制板干爆炸了?我们让大佬把led刷新间隔从16ms改成100ms,吃音问题瞬间没有了,无语了 。。。。。。。。。。。。。。。。。。。。 adx是一个控制板同时管理按键和led,为什么我没有遇到吃音问题呢,因为我的手台不是adx的... #dev

Hashtags

Results

找到 8 条相似帖子

搜索 #seaaccess

当前筛选 #seaaccess清除筛选
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #53539 · 2026/04/14 17:48

“ከሁለት፣ ሦስት ዓመት በፊት ለአያሌ መንግሥታት የባሕር ላይ እንቅስቃሴ አደጋ ሊገጥመው ይችላል፤ በዚህ ውስጥ ሚና አልባ ሆነን ከቆየን 130 ሚሊዮን ሕዝብ አደጋ ውስጥ ይወድቃል የሚል አቋም እናነሣ ነበር። በወቅቱ ምንም ነገር ስላልነበረ እምብዛም ተቀባይነት አልነበረውም። አሁን ግን ብዙዎች እያመኑበት ያለ ጉዳይ ነው። ከባህር መራቅ የባህርን ወይም የየብስን ትራንስፖርት ወይም የአየርን ትራንስፖርት ‘ግዴለም፤ በቀላሉ አገኘዋለሁ’ ብሎ ማሰብ የማይቻልበት ሁኔታ እየተፈጠረ ነው።” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) #EBC#Ethiopia#SeaAccess

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #53579 · 2026/04/15 18:33

“ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤት ካልሆነች አታድግም ብቻ ሳይሆን ሰፈሩ አይለወጥም፤ ሰፈሩ ሰላም አያገኝም፤ የዓለም ንግድም ይስተጓጎላል።” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) #EBC#Ethiopia#PMAbiyAhmed#SeaAccess

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #53541 · 2026/04/14 18:36

የባሕር በር ደኅንነት ጉዳይ ከምንጊዜውም በላይ አንገብጋቢ ሆኗል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ******************* የዓለም የንግድ እና የኢንዱስትሪ ትሥሥር በአየር፣ በየብስ እና በባሕር ሎጂስቲክስ ስጋቶች ውስጥ መውደቁን ተከትሎ የባሕር በር ደኅንነት ጉዳይ ከምንጊዜውም በላይ አንገብጋቢ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት፣ መንግሥት ከዓመታት በፊት የባሕር ላይ እንቅስቃሴ አደጋ ሊገጥመው እንደሚችል በመተንበይ "ከባሕር ከራቅን 130 ሚሊዮን ሕዝብ አደጋ ውስጥ ይወድቃል" የሚል የጸና አቋም ሲያራምድ ቆይቷል። ምንም እንኳን በወቅቱ ለዚህ ጉዳይ በቂ ትኩረት ባይሰጠውም፣ አሁን ላይ ግን ሀገራት የንግድ መስመሮችን ለጥቅማቸውም ሆነ ተቀናቃኞቻቸውን ለመጉዳት ሲሉ በከፍተኛ ደረጃ እየተቆጣጠሩት ይገኛሉ። በመሆኑም ከባሕር መራቅም ሆነ በአንድ መስመር ላይ ብቻ ጥገኛ መሆን አዋጭ ባለመሆኑ፣ ኢትዮጵያ ለዚህ የሎጂስቲክስ አለመረጋጋት አስቀድሞ መተንበይን ‘ፕሮአክቲቭ የሆነ መፍትሔ’ መከተሏን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል። #EBC#Ethiopia#PMAbiyAhmed#SeaAccess

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #53912 · 2026/04/23 18:08

አድማስን ፍለጋ፦ የመላ ኢትዮጵያውያን የጋራ አጀንዳ!! ***************** የባህር በር ለአንድ ሀገር መተንፈሻ ሳንባ ነው። ሳንባው የታፈነ ሰው በሩጫ ተወዳድሮ ሊያሸንፍ እንደማይችል ሁሉ ኢትዮጵያም ዛሬ ዛሬ በየገበያው የምናየው የሸቀጦች ዋጋ መናር፣ የሎጂስቲክስ መጓተትና የኑሮ ውድነት ሰንሰለቱ ሲመረመር መጨረሻው የሚገናኘው ከባህር መራቃችን እና መታነቃችን ጋር ነው። በመሆኑም የባህር በር ፍለጋው የጥቂቶች አጀንዳ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያውያን የፍትህ ጥሪ ነው። በአዶኒያስ ወልደአረጋይ #Ethiopia#SeaAccess#RedSea#EBC https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid07A7EMTS2gbwxuea9kdbkBGNTynJeikQu7h7bLw28KQYk9joN5XN3fVymLgywL9SQl

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #52755 · 2026/03/27 16:28

‎ኢትዮጵያ ወደ ባሕር መመለሷ ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው ********************* ኢትዮጵያ የቀይ ባሕር ገዥ፣ የአዱሊስ ወደብ ባለቤትና የገዘፈ የባሕር ኃይል ታሪክ ያላት ሀገር ነበረች። ዛሬ ግን በዓለም ላይ ወደብ ከሌላቸው ሀገራት መካከል በሕዝብ ብዛት ቀዳሚ ሆና መገኘቷ የታሪክ ምጸት ብቻ ሳይሆን፣ የክፍለ ዘመኑ ትልቁ የፖለቲካ ሴራ ውጤት ነው። ለምን ታነቅን? ቢባል ታዲያ መልሱ “በታሪክ አሻጥር ምክንያት” የሚል ነው። የቅኝ ገዥዎች ተንኮል እና በ1983ቱ የሥልጣን ሽግግር ወቅት የታየው የዲፕሎማሲ ዳተኝነት፣ የፖለቲካ ሴራ እና ታሪክ ይቅር የማይለው ስህተት ሀገራችንን በአንድ ጀምበር የባሕር በሯን እንድታጣ አደረጋት። በዚህም ምክንያት በየዓመቱ ለወደብ ኪራይ የምንገብረው 2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ እና 95% በጅቡቲ ላይ ጥገኛ መሆናችን፣ የሀገራችንን ዕድገት እና ብሔራዊ ደኅንነት አደጋ ላይ ጥሎታል። ኢትዮጵያ ወደ ባሕር የመመለስ ጥያቄዋ በጉልበት ሳይሆን በታሪክ እና በዓለም አቀፍ የባሕር ሕግ (UNCLOS) መሠረት የመጠቀም መብትን የተመረኮዘ ነው። የቅኝ ግዛት ውሎች እና ያለፉት ትውልዶች ስህተት የ130 ሚሊዮን ሕዝብን የኅልውና መብት ሊቀብሩት አይገባም። ከሴራ ማነቆ ተላቅቆ ወደ ባሕር አድማስ መሻገር፣ ለነገዋ የበለጸገች ኢትዮጵያ የሚከፈል ትልቁ ዋጋ ነው። "ያለፉት ትውልዶች በውጭ ሴራ እና በራሳቸው ቸልተኝነት የዘጉብንን የባሕር በር፣ ዛሬ በምን ዓይነት ብልሃትና ዲፕሎማሲ እናስመልስ?" ይህ የአሁኑ ትውልዱ ሊመልሰው የሚገባው ታሪካዊ ኃላፊነት ነው። አስተያየት መስጫው ውስጥ ያለው ሊንክ ይህ ሐሳብ በሰፊው የተተነተነበት ጽሑፍ ይዟል፤ እንዲያደነብቡት ጋብዘንዎታል። በአዶኒያስ ወልደአረጋይ #Ethiopia#SeaAccess#RedSea#NoMoreLandLocked

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #51920 · 2026/02/25 12:27

ከዓድዋ እስከ ሕዳሴ፤ ከሕዳሴ እስከ ባሕር በር! ********************** ዓድዋ ለእኛ ተራራን የመናድ፣ የማይቻለውን የመቻል እና የአንድነት ትልቅ ማህተማችን ነው። ያ ትናንት በዓድዋ ተራራዎች ላይ የነደደው የድል መንፈስ፣ ዛሬም በደምስራችን ውስጥ አለ! ትናንት፦ በዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ፋና ሆንን። ዛሬ፦ ያው የማይበገረው የዓድዋ መንፈስ ታላቁን የሕዳሴ ግድባችንን ዳር አደረሰ። በስንዴ ሉዓላዊነት ታሪክ ተሠራ፤ የዓባይን ወንዝ ለብርሃን እና ለብልፅግና አዋልነው። ነገ፦ ቀጣዩ የታሪክ ምዕራፍ ተጀምሯል፤ የባሕር በር ጉዳይ የሕልውናችን፣ የኢኮኖሚ ነፃነታችን እና የትውልድ ጥያቄ ነው። ትናንት በጋራ ቆመን ያላሸነፍነው ፈተና የለም፤ ዛሬም በዚያው በዓድዋ ፅናት እና በሕዳሴው ወኔ የባሕር በር ጥያቄያችንን በድል እንደምናጠናቅቅ ጥርጥር የለውም! ታሪክ ይደገማል! ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነት ከፍ ብላ ትቀጥላለች! #Ethiopia#AdwaSpirit#GERD#SeaAccess#የሕዳሴግድብ#የባሕርበር#EBC