TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← () => "翠楼屋"

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

查找相似内容

Source channel @lambdaexpression · Post #299 · 1月17日

市中继好像和广州黄埔的中继撞下行频率了,我在我家能同时收到两个中继的下行 一个S4一个S2 #ham

Hashtags

Results

找到 1 条相似帖子

搜索 #budgetallocation

当前筛选 #budgetallocation清除筛选
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #51894 · 2026/02/23 07:28

ለክልሎች የሚተላለፍ የጋራ ገቢ መጠን እያደገ መጥቷል - አቶ አገኘሁ ተሻገር *************** ለክልሎች የሚተላለፈው የጋራ ገቢ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መምጣቱን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር አስታወቁ። ምክር ቤቱ በገቢዎች ሚኒስቴር እና በማዕድን ሚኒስቴር ተሰብስቦ በቀመሩ መሠረት የሚተላለፈው የክልሎች ድርሻ በትክክል መድረሱን ለማረጋገጥ በተከናወነ የፋይናንስና ሕጋዊነት ኦዲት ግኝት ላይ የውይይት መድረክ አካሂዷል። በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፤ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የሚሰበሰበው የጋራ ገቢ ለክልሎች ለማስተላለፍ የሚሰላበት ቀመር ማሻሻያ እንደተደረገበት አስታውሰዋል። ከማሻሻያው አስቀድሞ ክልሎች ከጋራ ገቢ የሚያገኙት ድርሻ 4.2 ቢሊዮን ብር ብቻ እንደነበረ ጠቁመው፤ አሁን ላይ መጠኑ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ገልጸዋል። እንደ አፈ-ጉባኤው ማብራሪያ፣ በ2017 በጀት ዓመት ብቻ ከጋራ ገቢ ለክልሎች የሚከፋፈለው ድርሻ 91.73 ቢሊዮን ብር ደርሷል። በተያዘው የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሰባት ወራት ውስጥ ብቻ ከ71 ቢሊዮን ብር በላይ ማከፋፈል መቻሉ በመድረኩ ተመልክቷል። የውይይት መድረኩ በኦዲት ግኝት ሪፖርቱ ላይ በዝርዝር በመምከር፣ የሀብት ክፍፍሉ ፍትሐዊነትና ሕጋዊነትን ይበልጥ ለማረጋገጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚቀጥል ታውቋል። በሳምሶን ገድሉ #EthiopianBroadcastingCorporation#Ethiopia#HouseOfFederation#BudgetAllocation#RegionalRevenue