TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← () => "翠楼屋"

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

查找相似内容

Source channel @lambdaexpression · Post #299 · 1月17日

市中继好像和广州黄埔的中继撞下行频率了,我在我家能同时收到两个中继的下行 一个S4一个S2 #ham

Hashtags

Results

找到 1 条相似帖子

搜索 #proclamation

当前筛选 #proclamation清除筛选
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #53835 · 2026/04/21 13:26

የፌዴራል የስፖርት ልማት እና አስተዳደር አዋጅ በሙሉ ድምፅ ጸደቀ ********************* የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ስብሰባ፣ የስፖርት ዘርፍ ላይ መሠረታዊ ለውጥ ያመጣል ተብሎ የታመነበትን የፌዴራል የስፖርት ልማት እና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ መርምሮ አጽድቋል። አዲሱ አዋጅ ቁጥር 1413/2018 በስፖርቱ ዘርፍ አካታች፣ ዘመናዊና ግልጽነት ያለው የአሰራር ሥርዓት ለመዘርጋት ምቹ መደላድል የሚፈጥር ሲሆን፣ በዘርፉ የሚታዩ የአሰራርና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ታላቅ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል። አዋጁ የስፖርት መሠረተ ልማቶችንና ማሰልጠኛ ተቋማትን ከማስፋፋት ባለፈ፣ የስፖርት ግብዓት አምራቾች እንዲበረታቱና ዘርፉ ለሀገር ኢኮኖሚ የራሱን ድርሻ እንዲያበረክት ያደርጋል። በተጨማሪም ማህበራዊ ትስስርን በማጎልበት፣ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን በማጠናከር እና ስፖርት ነክ ወንጀሎችን በመከላከል ረገድ ጉልህ ሚና እንደሚጫወት በምክር ቤቱ የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወርቀሰሙ ማሞ አብራርተዋል። የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ በሰጡት ማብራሪያ፣ ስፖርት የኢትዮጵያውያን የኩራት ምንጭ እንዲሆን ዘርፉን የያዙ ማነቆዎችን በአሰራርና በስርዓት መፍታት የግድ እንደሚል ጠቁመዋል። አዋጁ ከዘርፉ ማግኘት ያለባትን ጥቅም እንድታገኝ በማድረግ ረገድ መሠረታዊ ለውጥ እንደሚያመጣ ሚኒስትሯ ገልጸዋል። የምክር ቤቱ አባላትም የአዋጁን አስፈላጊነት በማመንና አፈጻጸሙ ላይ ትኩረት እንዲደረግ በማሳሰብ አዋጁን በሙሉ ድምፅ ማጽደቁን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል። #EthiopianBroadcastingCorporation#Ethiopia#SportsDevelopment#Parliament#Proclamation#EthiopianSports