TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← () => "翠楼屋"

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

查找相似内容

Source channel @lambdaexpression · Post #310 · 2月13日

by iPhone13 Pro #摄影

Hashtags

Results

找到 2 条相似帖子

搜索 #asellawindfarm

当前筛选 #asellawindfarm清除筛选
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #53654 · 2026/04/16 20:38

የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ፣ ግብርናን ለማዘመን እና የገበያ ትስስር ለመፍጠር ያለው ፋይዳ የጎላ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ********************* ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ምርቃት ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የልማት ዝርጋታና የኢነርጂ አማራጮች ለአካባቢው አርሶ አደሮች የኑሮ ጥራት መሻሻልና ለኢኮኖሚ ዕድገት ያላቸውን ፋይዳ አብራርተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለአሰላ፣ ለአርሲ እና ለአጎራባች የምስራቅ ሸዋ ነዋሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት፣ አርሲ በእርሻ ምርታማነቱ ቢታወቅም፣ የነበረበት የውስጥ ለውስጥ መንገድ እጥረት ትልቅ ፈተና መሆኑን አንስተዋል። አዲሱ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የገነባው ከ27 ኪሎ ሜትር በላይ መንገድ ለንፋስ ኃይል ማመንጫው ግልጋሎት ከመስጠት ባሻገር ለአካባቢው ግብርና መዘመን መሠረት የሚጥል መሆኑን ገልጸዋል። መንገዱ ከኮምባይነሮችና ትራክተሮች በተጨማሪ ትራንስፖርትን ተደራሽ በማድረግ ምርትን በፍጥነት ወደ ማዕከላዊ ገበያ ለማድረስ ያግዛል ብለዋል። የአርሶ አደሩ ምርት እንዳለ ለገበያ ከመቅረብ ይልቅ በቅርብ ርቀት በሚገኙ አግሮ-ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪዎች ገብቶ፣ ተቀናብሮ፣ እሴት ተጨምሮበት እንዲወጣ በማድረግ የተሻለ ገቢ ለማስገኘት እንደሚሠራ ገልጸዋል። በየአካባቢው በመንግሥት የተጀመሩ በርካታ ፕሮጀክቶች ከፍተኛ ክትትል እየተደረገላቸው በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኙ አውስተው፤ ለኢትዮጵያ ብልጽግና መሠረት የመጣሉ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። በንፍታሌም እንግዳወርቅ #Ethiopia#Arsi#AsellaWindFarm#EthiopiaDelivers#AbiyAhmed#EBC

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #53613 · 2026/04/16 11:22

ኢትዮጵያ ጨለማን ለመግፈፍና በንፋስ ኃይል ብርሃን እየፈጠረች ነው ************** ኢትዮጵያ ጨለማን ለመግፈፍና በንፋስ የብርሃን መንገድ ለመራመድ በአሸጎዳ፣ አዳማና አይሻ የጀመረችውን ጉዞ አሁን አሰላ ላይ ደግማዋለች። ይህን አስመልክተው መልዕክት ያስተላለፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያም ሆነች አፍሪካ በ21ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽና ከዚያ በኋላ የሚመኙት ዕድገት ተፈጥሮን በማይጎዳና ከተፈጥሮ ጋር በስምምነት የሚከናወን መሆኑን ያሳያል ብለዋል። ፕሮጀክቱ 100 ሜጋ ዋት ንጹሕ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጭ ሲሆን፣ እያንዳንዳቸው 3.46 ሜጋ ዋት ኃይል የሚያመነጩ 29 ተርባይኖች አሉት። ሙሉ ዜናውን… https://web.facebook.com/share/p/1CaDVyfbGU/ #Ethiopia#CleanEnergy#WindPower#AsellaWindFarm#GreenEnergy#Sustainability