TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← () => "翠楼屋"

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

查找相似内容

Source channel @lambdaexpression · Post #310 · 2月13日

by iPhone13 Pro #摄影

Hashtags

Results

找到 1 条相似帖子

搜索 #debtrestructuring

当前筛选 #debtrestructuring清除筛选
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #51603 · 2026/02/11 17:14

ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያዋን የሚደግፉ ቁልፍ ስምምነቶችን ከፈረንሳይ ጋር ተፈራረመች *********** ዛሬ በአዲስ አበባ በተከናወነ ሥነ-ሥርዓት፣ የኢትዮጵያና የፈረንሳይ መንግሥታት የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ማሻሻያ የሚደግፉ ቁልፍ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ እንዲሁም በፈረንሳይ የአውሮፓና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሚስዝ ኤሌኖሬ ካሮይት መንግሥታቱን በመወከል ተፈራርመዋል። የስምምነቱ ዋና ዋና ይዘቶች፦ 1. የዕዳ ሽግሽግ (Debt Restructuring): በG20 የጋራ ማዕቀፍ ስር ከሁለትዮሽ አበዳሪዎች ጋር የተደረገ የመጀመሪያው ታሪካዊ የዕዳ ሽግሽግ ስምምነት ተፈርሟል። ይህም ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማገገም ትልቅ ሚና ይጫወታል። 2. የ81.5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ፦ ለሁለተኛው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ (HGER 2.0) ማስፈጸሚያ የሚውል 80 ሚሊዮን ዩሮ የበጀት ድጋፍ እና 1.5 ሚሊዮን ዩሮ የቴክኒክ ድጋፍ ስምምነት ተደርጓል። 3. አዳዲስ የኢንቨስትመንት መስኮች፦ ፈረንሳይ በኢትዮጵያ በሚገነባው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት አሳይታለች። 4. ትብብርን ማስፋት፦ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለው የፈረንሳይ አጠቃላይ የኢንቨስትመንት መጠን ከ600 ሚሊዮን ዩሮ በላይ የደረሰ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነው (300 ሚሊዮን ዩሮ) ለኢነርጂ ዘርፍ መዋል መቻሉ ተገልጿል። ይህ ስምምነት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የቆየ ወዳጅነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግርና የኢትዮጵያን የንግድና የኢኮኖሚ ተወዳዳሪነት የሚያሳድግ መሆኑ ተመልክቷል። በሀብተሚካኤል ክፍሉ #Ethiopia#France#StrategicPartnership#DebtRestructuring#EconomicReform#EBC#EthiopianBroadcastingCorporation