TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← () => "翠楼屋"

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

查找相似内容

Source channel @lambdaexpression · Post #310 · 2月13日

by iPhone13 Pro #摄影

Hashtags

Results

找到 1 条相似帖子

搜索 #developmentandpeace

当前筛选 #developmentandpeace清除筛选
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #52024 · 2026/03/04 12:00

የወቅቱ አርበኝነት የባሕር በር ጥያቄን ማሳካት ነው ************* 130ኛው የዓድዋ ድል በዓል በሲዳማ ክልል ''ከአኩሪ ታሪክ ወደ ብሩህ አድማስ'' በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል። በመድረኩ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ አርበኞች፣ የፀጥታ አካላት፣ ሴቶችና ወጣቶች ተገኝተዋል። የሲዳማ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ በየነ በራሳ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዓድዋ የትናንት፣ የዛሬ እና የነገ ትውልድን ያስተሳሰረ የቃል ኪዳን ምልክት መሆኑን ገልጸዋል። ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም፣ የኢትዮጵያውያን የወቅቱ አርበኝነት ከድህነት መውጫ የሆነውን የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄን ማሳካት መሆኑን በመጥቀስ፤ የአሁኑ ትውልድ እንደ ባሕር በር ያሉ ብሔራዊ ጥቅሞችን ለማስከበር በጋራ መቆም እንዳለበት አሳስበዋል። የክልሉ ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እመቤት ኢሳያስ በበኩላቸው፤ ዓድዋ የኅብረት እና የአንድነት ምልክት መሆኑን ገልጸዋል። ወጣቶችና ሴቶች ዛሬም ለሀገር ሰላምና ለልማት በአርበኝነት ሊቆሙ እንደሚገባም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። በበዓሉ አከባበር ላይ የታደሙት የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችም የጀግኖች አባቶችን ታሪክ በማስታወስ፣ ለሀገራዊ አንድነትና ለልማት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ቃል ገብተዋል። በአስረሳው ወገሼ #የዓድዋድል#VictoryOfAdwa#ብሔራዊጥቅም#NationalInterest#አርበኝነት#DevelopmentAndPeace