TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← () => "翠楼屋"

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

查找相似内容

Source channel @lambdaexpression · Post #310 · 2月13日

by iPhone13 Pro #摄影

Hashtags

Results

找到 1 条相似帖子

搜索 #josephboakai

当前筛选 #josephboakai清除筛选
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #53509 · 2026/04/14 14:49

ኢትዮጵያና ላይቤሪያ ከጋራ የጽናት ታሪክ የሚመነጭ ጥልቅ ግንኙነት አላቸው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) *********************** ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይን በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት አቀባበል አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ኢትዮጵያ የገቡትን የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት አቀባበል በማድረጌ ታላቅ ክብር ይሰማኛል ብለዋል። ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በቅኝ ግዛት ያልተገዙ፣ ለአኅጉሩ ነፃነትና አንድነት ድምፅ በመሆን ከጋራ የጽናት ታሪክ የሚመነጭ ጥልቅና ዘመናትን የተሻገረ ግንኙነት እንዳላቸውም አስታውቀዋል። ዛሬም እንደ ሁሌው ኢትዮጵያ ከሰፊ ገበታዋ ያላትን ታላቅ ዐቅምና ዘላቂ ወዳጅነት፣ አብረዋት ለሚጓዙ ሁሉ ለማካፈል ዝግጁ መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል። በዚህ መንፈስ ይህ ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በማጠናከር፤ የጋራ ህልሞቻችንን በማይናወጥ መሠረት እና የመፈጸም ቁርጠኝነት ወሳኝ ምዕራፍ እንደሚሆን ጽኑ እምነት እንዳላቸውም ገልጸዋል። #EBC#Ethiopia#Liberia#Diplomacy#AbiyAhmed#JosephBoakai#PanAfricanism#BilateralRelations