TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← () => "翠楼屋"

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

查找相似内容

Source channel @lambdaexpression · Post #310 · 2月13日

by iPhone13 Pro #摄影

Hashtags

Results

找到 2 条相似帖子

搜索 #militaryexcellence

当前筛选 #militaryexcellence清除筛选
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #51256 · 2026/01/24 05:45

የኢትዮጵያ አየር ኃይል - የቴክኖሎጂ ልህቀት 🔥🔥🔥 ************* 🚀 እጅግ ዘመናዊ ሰው አልባ አውሮፕላኖች (Drones) ባለቤት! 👩‍🚀የአየር ላይ ውጊያ የበላይነትን ማረጋገጥ የሚችል የሰው ኃይል እና ትጥቅ! ☀️⛈️ በማንኛውም የአየር ጠባይ ግዳጅ መፈጸም የሚችል ብቃት! የኢትዮጵያ አየር ኃይል - ሁሌም በተጠንቀቅ!! #ebcdotstream#Ethiopia#ethiopianairforce#airforce90#techinnovation#militaryexcellence

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #51274 · 2026/01/25 20:58

የጠላት ጄቶችን አየር ላይ ያጋጩት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ - ብርጋዴር ጄኔራል ለገሰ ተፈራ! 🇪🇹✈️ ************ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን አስከብራ የኖረችው እንደ ብርጋዴር ጄኔራል ለገሰ ተፈራ ባሉ የማይበገሩ ጀግኖች መስዋዕትነት ነው። የአየር ኃይላችን የ90 ዓመት ጉዞ ሲታሰብ፣ የነዚህ "የሰማይ ንስሮች" ታሪክ ምንጊዜም በደማቁ ይነሳል። የጄኔራል ለገሰ አስደናቂ የጀግንነት ታሪክ፦ 💥 የአየር ላይ ጀብዱ፦ በኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት ወቅት (1969-70 ዓ.ም) ‘F5-E' የጦር ጄትን በማብረር፣ 2 የጠላት ‘ሚግ 21' ጄቶችን አየር ላይ እርስ በርስ እንዲጋጩ በማድረግና ሌሎች በርካታ ጄቶችን በመጣል የማይረሳ ታሪክ ሠርተዋል። 📚 የታሪክ ምስክርነት፦ ኦስትሪያዊው የታሪክ አጥኚ ቶም ኩፐር ‘Wings over Ogaden' በተሰኘ መጽሐፉ፤ የኢትዮጵያ አብራሪዎች በቁጥር ቢበለጡም በላቀ ክህሎታቸው ፍጹም የአየር ላይ የበላይነት እንደነበራቸው መስክሯል። 💪 ጽናትና መስዋዕትነት፦ በድሉ ዋዜማ በፊልቱ ግንባር ጄታቸው ተመትታ በፓራሹት ወርደው በጠላት እጅ ወደቁ። ይህን ተከትሎ ለ11 ዓመታት በሶማሊያ እስር ቤት አሰቃቂ ስቃይ ቢደርስባቸውም፤ ይህ ለሀገራቸው የነበራቸውን ፍቅር ሊያጠፋው አልቻለም። 🏅 የክብር ሽልማት፦ ከእስር ተመልሰው ሀገራቸው ሲገቡ በወቅቱ የሀገሪቱ ከፍተኛ የክብር ሽልማት የነበረውን "የኅብረተሰብዓዊት ኢትዮጵያ ወደር የለሽ ጀግና ሜዳይ" ተሸልመዋል። ዛሬም የአየር ኃይላችን ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ታጥቆ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ሲቆም፣ የእነዚህ ጀግኖች ታሪክ ለትውልዱ ትልቅ የሞራል ስንቅ ነው። #EBCDotstream#Ethiopia#EthiopianAirForce#LegesseTefera#Hero#AviationHistory#ETAF90#NationalPride#MilitaryExcellence ሙሉ ዘገባውን እዚህ ያገኙታል።