ኢሕአፓ የፓርቲ አባሉ መታሰሩን ገለፀ። የጋሞ ዞን የኢሕአፓ ሰብሳቢ እና የአርባ ምንጭ ከተማ የትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ፓርላማ እጩ አቶ ሰለሞን ሳዳ በጸጥታ አካላት ታስረው መለቀቃቸውን የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። ፓርቲው በትብብሩ፣ በምርጫ ቦርድ ብርቱ ክትትል ከሰዓታት የአፈና እስር በኋላ መለቀቃቸውን በመግለፅ፣ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን አመስግኗል። አቶ ሰለሞን በሌሊት ታፍነው መውረዳቸውን የገለፀው ኢህአፓ፣ እጩው ያለመከሰስ መብት ያለው መሆኑን የዞኑ ሰብሳቢም እንደሆነ አስታውቋል። የመንግስት ካድሬዎች ራሱን ከእጩነት እንዲያገል ከዚህ በፊት በንብረቶቹ ላይ የማቃጠል አደጋ አድርሰውበት ነበር ተብሏል። የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ-ኢህአፓ እጩዎችን በዚህ መንገድ ማሰር፣ ማስፈራራት ተጠናክሮ መቀጠሉ እንደሚያሳዝነው ገልጿል። ከዚህ በፊት አባላቶቹ በተደጋጋሚ መታሰራቸውን ያስታወቀው ፓርቲው፣ የፓርቲ እጩዎችን እያሰሩ፣ እያስፈራሩ መልቀቅ እና ማሳደድ ጤናማ አይደለም ሲል ተቃውሟል። #Ethiopia#news#EPRP#ዜና#NationalElection#EthiopianPolitics
TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
by iPhone13 Pro #摄影
Hashtags
Results
找到 2 条相似帖子
搜索 #nationalelection
当前筛选 #nationalelection清除筛选
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
@ebcnewsnow · Post #52107 · 2026/03/06 12:37
የፖሊሲ አማራጮች ክርክር፦ የግብርናው ዘርፍ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ********************** ኢዜማ፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲ፣ ኢሶዴፓ እና ብልፅግና ፓርቲ በሀገሪቱ የግብርና ፖሊሲ ዙሪያ የሚያደርጉትን ጥልቅ ክርክር ነገ ቅዳሜ ምሽት በኢቢሲ (EBC) ይጠብቁ። የትኛው ፓርቲ ለኢትዮጵያ ግብርና የተሻለ መፍትሔ አለው? ነገ ምሽት እንዳያመልጥዎ #Ethiopia#NationalElection#AgriculturePolicy#EBC#Debate#ምርጫ2018