🇷🇺 сухур и ифтар в Бишкеке www.flytezjet.com 🇰🇬 Бишкектеги сухур жана ифтар www.flytezjet.com #Ramadan2026#Bishkek#Kyrgyzstan#TezJet#FlyTezJet
by iPhone13 Pro #摄影
Hashtags
找到 5 条相似帖子
搜索 #ramadan2026
@alaport_tav · Post #401 · 2026/02/19 05:22
🌙 Қасиетті Рамазан айының басталуымен құттықтаймыз! Ниеттеріңіз қабыл болып, жүздеріңіздегі нұр, жүректеріңіздегі иман арта берсін ✨ ⠀ Әр саяхатшының ең шулы терминалда да тыныштыққа бөленуіне және, әлбетте, асыға күтетін жандармен қауышуына тілектеспіз 🍲 ⠀ 🌙 Congratulations on the beginning of Ramadan! May this holy month bring joyful renewal and new hope ✨ ⠀ We wish every traveler to find their moment of peace - even in the busiest terminal. And of course, to arrive on time where loved ones are waiting to gather around the table together ⠀ 🌙 Поздравляем с началом Рамадана! Пусть этот священный месяц принесёт счастливое обновление и подарит новые надежды ✨ ⠀ Желаем каждому путнику найти свою точку тишины даже в самом оживленном терминале. И, конечно, вовремя добраться туда, где вас ждут за общим столом 🍲 ⠀ #Ramadan2026#ALAAlmatyInternationalAirport
@ebcnewsnow · Post #51706 · 2026/02/16 10:52
የረመዳን ጾም፣ ጨረቃ ነገ ምሽት ከታየች ረቡዕ፣ ካልሆነ ግን ሐሙስ ይጀምራል ************** የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 1447ኛው ታላቁ የረመዳን ጾምን ምክንያት በማድረግ በዛሬው ዕለት የመልካም ምኞት መግለጫ ሰጥቷል። የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ሼህ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ የፌደራል ሸሪዓ ፍርድ ቤት መረጃን ጠቅሰው እንዳሉት፤ የረመዳን ጾም መጀመሪያ ዕለት በጨረቃ መታየት ላይ የተመሠረተ ይሆናል። በዚሁ መሠረት ጨረቃ ነገ ማክሰኞ ምሽት ከታየች፣ የረመዳን ጾም ረቡዕ የካቲት 11 ይጀምራል። ጨረቃ ማክሰኞ ምሽት ካልታየች ግን፣ ጾሙ ሐሙስ የካቲት 12 ቀን እንደሚጀምር ገልጸዋል። ፕሬዚዳንቱ ረመዳን የአንድነት፣ የሰላም እና የኢባዳ (የአምልኮ) ወር መሆኑን ገልጸው፤ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ እንደ ሃይማኖቱ አስተምህሮ የተቸገሩ ወገኖችን በማገዝ እንዲያሳልፈው አደራ ብለዋል። በመጨረሻም ሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላም እንድትሆን እና ወደምትመኘው ሁለንተናዊ ብልጽግና እንድትሸጋገር ምዕመኑ በረመዳን ዱዓ እንዲያደርግ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። በዘሃራ መሃመድ #Ramadan2026#Ethiopia#IslamicAffairs#RamadanKareem#EthiopianBroadcastingCorporation
@ebcnewsnow · Post #52343 · 2026/03/12 18:15
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የኢፍጣር መርሐ ግብር ላይ ተሳተፉ ***************** ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) አዘጋጅነት በተከናወነው የኢፍጣር መርሐ ግብር ላይ በመገኘት ከመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች፣ ከኢንቨስትመንት አጋሮችና ከእምነቱ ተከታዮች ጋር በአንድነት አሳልፈዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በእስልምና አስተምህሮ አብሮ መብላትና መረዳዳት ትልቅ ሥፍራ የሚሰጠው እሴት መሆኑን ገልጸው፤ “ጎረቤቱ ርቦት እርሱ ጠግቦ የሚያድር ከኛ አይደለም” የሚለው የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) አስተምህሮ ለሰው ልጅ ክብር መስጠትን፣ ርኅራኄንና የጋራ ደስታን በተግባር መተርጎም እንደሚገባ የሚያሳይ ሕያው የሕይወት ስንቅ መሆኑን አብራርተዋል። የዕለቱ የኢፍጣር መርሐ ግብር የኢትዮጵያን የብዝኃነት ውበት፣ አብሮነትና አንድነት የሚያንጸባርቅ መሆኑን የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በኢኮኖሚው ዘርፍ የሚመዘገበው ስኬት ትርጉም የሚኖረው በታላቅ የፍቅርና የመተሳሰብ ሰንሰለት ተሳስረን ለትውልድ የምትተርፍ ጠንካራ ሀገርን በጋራ መገንባት ስንችል መሆኑን አስገንዝበዋል። ብልጽግና የሚረጋገጠው እንዲህ ባሉ የዳበሩ ማኅበራዊ እሴቶች ጭምር መሆኑን በመጠቆም ለሁሉም የእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም የረመዳንና የኢባዳ ጊዜ እንዲሆንላቸው ምኞታቸውን ገልጸዋል። #EBC#Ethiopia#TemesgenTiruneh#Iftar#Ramadan2026#UnityInDiversity
@ebcnewsnow · Post #52464 · 2026/03/18 15:16
ጨረቃ ዛሬ ባለመታየቷ 1447ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል ከነገ ወዲያ ይከበራል *************** የሸዋል ወር ጨረቃ ዛሬ ባለመታየቷ 1447ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል ከነገ ወዲያ አርብ መጋቢት 11 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚከበር ተገልጿል። የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሸህ ሙባረክ መሐመድ አወል ለኢቢሲ ዶትስትሪም እንደገለፁት፤ የሸዋል ወር ጨረቃ ዛሬ ባለመታየቷ 1447ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል ከነገ በስቲያ መጋቢት 11 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚከበር አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 1447ኛውን የኢድ አል ፊጥር በዓል አስመልክቶ ቀድሞ ብሎ ባስተላለፈው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፤ ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር ስለ ሀገር ሰላምና መረጋጋት ፈጣሪን በመማጸን እንዲሁም እስልምና ባዘዘው መሠረት በታላቅ ጨዋነትና ሥነ-ምግባር ሊሆን እንደሚገባም አሳስቧል። በላሉ ኢታላ #EBC#Ethiopia#EidAlFitr1447#IslamicCouncil#Shawwal#Ramadan2026#EidMubarak