“ከሁለት፣ ሦስት ዓመት በፊት ለአያሌ መንግሥታት የባሕር ላይ እንቅስቃሴ አደጋ ሊገጥመው ይችላል፤ በዚህ ውስጥ ሚና አልባ ሆነን ከቆየን 130 ሚሊዮን ሕዝብ አደጋ ውስጥ ይወድቃል የሚል አቋም እናነሣ ነበር። በወቅቱ ምንም ነገር ስላልነበረ እምብዛም ተቀባይነት አልነበረውም። አሁን ግን ብዙዎች እያመኑበት ያለ ጉዳይ ነው። ከባህር መራቅ የባህርን ወይም የየብስን ትራንስፖርት ወይም የአየርን ትራንስፖርት ‘ግዴለም፤ በቀላሉ አገኘዋለሁ’ ብሎ ማሰብ የማይቻልበት ሁኔታ እየተፈጠረ ነው።” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#EBC#Ethiopia#SeaAccess
የባሕር በር፡- የማይቀረው የትውልድ ድል!
#EthiopianBroadcastingCorporation#Ebcdotstream#Ethiopia#SeaAccess
“ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤት ካልሆነች አታድግም ብቻ ሳይሆን ሰፈሩ አይለወጥም፤ ሰፈሩ ሰላም አያገኝም፤ የዓለም ንግድም ይስተጓጎላል።” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#EBC#Ethiopia#PMAbiyAhmed#SeaAccess
“ኢትዮጵያን የባሕር በር አልቦ አድርጎ መቀጠል በየትኛውም ዘመን አዋጭ አይደለም” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#EBC#Ethiopia#PMAbiyAhmed#SeaAccess
የባሕር በር ደኅንነት ጉዳይ ከምንጊዜውም በላይ አንገብጋቢ ሆኗል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
*******************
የዓለም የንግድ እና የኢንዱስትሪ ትሥሥር በአየር፣ በየብስ እና በባሕር ሎጂስቲክስ ስጋቶች ውስጥ መውደቁን ተከትሎ የባሕር በር ደኅንነት ጉዳይ ከምንጊዜውም በላይ አንገብጋቢ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት፣ መንግሥት ከዓመታት በፊት የባሕር ላይ እንቅስቃሴ አደጋ ሊገጥመው እንደሚችል በመተንበይ "ከባሕር ከራቅን 130 ሚሊዮን ሕዝብ አደጋ ውስጥ ይወድቃል" የሚል የጸና አቋም ሲያራምድ ቆይቷል።
ምንም እንኳን በወቅቱ ለዚህ ጉዳይ በቂ ትኩረት ባይሰጠውም፣ አሁን ላይ ግን ሀገራት የንግድ መስመሮችን ለጥቅማቸውም ሆነ ተቀናቃኞቻቸውን ለመጉዳት ሲሉ በከፍተኛ ደረጃ እየተቆጣጠሩት ይገኛሉ።
በመሆኑም ከባሕር መራቅም ሆነ በአንድ መስመር ላይ ብቻ ጥገኛ መሆን አዋጭ ባለመሆኑ፣ ኢትዮጵያ ለዚህ የሎጂስቲክስ አለመረጋጋት አስቀድሞ መተንበይን ‘ፕሮአክቲቭ የሆነ መፍትሔ’ መከተሏን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል።
#EBC#Ethiopia#PMAbiyAhmed#SeaAccess
አድማስን ፍለጋ፦ የመላ ኢትዮጵያውያን የጋራ አጀንዳ!!
*****************
የባህር በር ለአንድ ሀገር መተንፈሻ ሳንባ ነው።
ሳንባው የታፈነ ሰው በሩጫ ተወዳድሮ ሊያሸንፍ እንደማይችል ሁሉ ኢትዮጵያም ዛሬ ዛሬ በየገበያው የምናየው የሸቀጦች ዋጋ መናር፣ የሎጂስቲክስ መጓተትና የኑሮ ውድነት ሰንሰለቱ ሲመረመር መጨረሻው የሚገናኘው ከባህር መራቃችን እና መታነቃችን ጋር ነው።
በመሆኑም የባህር በር ፍለጋው የጥቂቶች አጀንዳ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያውያን የፍትህ ጥሪ ነው።
በአዶኒያስ ወልደአረጋይ
#Ethiopia#SeaAccess#RedSea#EBC
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid07A7EMTS2gbwxuea9kdbkBGNTynJeikQu7h7bLw28KQYk9joN5XN3fVymLgywL9SQl
ኢትዮጵያ ወደ ባሕር መመለሷ ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው
*********************
ኢትዮጵያ የቀይ ባሕር ገዥ፣ የአዱሊስ ወደብ ባለቤትና የገዘፈ የባሕር ኃይል ታሪክ ያላት ሀገር ነበረች።
ዛሬ ግን በዓለም ላይ ወደብ ከሌላቸው ሀገራት መካከል በሕዝብ ብዛት ቀዳሚ ሆና መገኘቷ የታሪክ ምጸት ብቻ ሳይሆን፣ የክፍለ ዘመኑ ትልቁ የፖለቲካ ሴራ ውጤት ነው።
ለምን ታነቅን? ቢባል ታዲያ መልሱ “በታሪክ አሻጥር ምክንያት” የሚል ነው። የቅኝ ገዥዎች ተንኮል እና በ1983ቱ የሥልጣን ሽግግር ወቅት የታየው የዲፕሎማሲ ዳተኝነት፣ የፖለቲካ ሴራ እና ታሪክ ይቅር የማይለው ስህተት ሀገራችንን በአንድ ጀምበር የባሕር በሯን እንድታጣ አደረጋት።
በዚህም ምክንያት በየዓመቱ ለወደብ ኪራይ የምንገብረው 2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ እና 95% በጅቡቲ ላይ ጥገኛ መሆናችን፣ የሀገራችንን ዕድገት እና ብሔራዊ ደኅንነት አደጋ ላይ ጥሎታል።
ኢትዮጵያ ወደ ባሕር የመመለስ ጥያቄዋ በጉልበት ሳይሆን በታሪክ እና በዓለም አቀፍ የባሕር ሕግ (UNCLOS) መሠረት የመጠቀም መብትን የተመረኮዘ ነው።
የቅኝ ግዛት ውሎች እና ያለፉት ትውልዶች ስህተት የ130 ሚሊዮን ሕዝብን የኅልውና መብት ሊቀብሩት አይገባም።
ከሴራ ማነቆ ተላቅቆ ወደ ባሕር አድማስ መሻገር፣ ለነገዋ የበለጸገች ኢትዮጵያ የሚከፈል ትልቁ ዋጋ ነው።
"ያለፉት ትውልዶች በውጭ ሴራ እና በራሳቸው ቸልተኝነት የዘጉብንን የባሕር በር፣ ዛሬ በምን ዓይነት ብልሃትና ዲፕሎማሲ እናስመልስ?"
ይህ የአሁኑ ትውልዱ ሊመልሰው የሚገባው ታሪካዊ ኃላፊነት ነው።
አስተያየት መስጫው ውስጥ ያለው ሊንክ ይህ ሐሳብ በሰፊው የተተነተነበት ጽሑፍ ይዟል፤ እንዲያደነብቡት ጋብዘንዎታል።
በአዶኒያስ ወልደአረጋይ
#Ethiopia#SeaAccess#RedSea#NoMoreLandLocked
ከዓድዋ እስከ ሕዳሴ፤ ከሕዳሴ እስከ ባሕር በር!
**********************
ዓድዋ ለእኛ ተራራን የመናድ፣ የማይቻለውን የመቻል እና የአንድነት ትልቅ ማህተማችን ነው።
ያ ትናንት በዓድዋ ተራራዎች ላይ የነደደው የድል መንፈስ፣ ዛሬም በደምስራችን ውስጥ አለ!
ትናንት፦ በዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ፋና ሆንን።
ዛሬ፦ ያው የማይበገረው የዓድዋ መንፈስ ታላቁን የሕዳሴ ግድባችንን ዳር አደረሰ። በስንዴ ሉዓላዊነት ታሪክ ተሠራ፤ የዓባይን ወንዝ ለብርሃን እና ለብልፅግና አዋልነው።
ነገ፦ ቀጣዩ የታሪክ ምዕራፍ ተጀምሯል፤ የባሕር በር ጉዳይ የሕልውናችን፣ የኢኮኖሚ ነፃነታችን እና የትውልድ ጥያቄ ነው።
ትናንት በጋራ ቆመን ያላሸነፍነው ፈተና የለም፤ ዛሬም በዚያው በዓድዋ ፅናት እና በሕዳሴው ወኔ የባሕር በር ጥያቄያችንን በድል እንደምናጠናቅቅ ጥርጥር የለውም!
ታሪክ ይደገማል! ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነት ከፍ ብላ ትቀጥላለች!
#Ethiopia#AdwaSpirit#GERD#SeaAccess#የሕዳሴግድብ#የባሕርበር#EBC